የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በአክሱም ያደረገውን ስብሰባ አጠናቀቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

በአክሱም ከተማ ሲካሄድ የነበረው አከራካሪው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መጠናቀቁ ተገልጿል። በስብሰባው ማጠናቀቂያ ላይ ኮሚቴው ያስለለፋቸው ውሳኔዎች በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሸጋግሩ እንደሚችሉ ተገምቷል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው በጄነራል ታደሰ ወረደ የሚመራውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደማይቀበል አስታውቋል።

በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መካከል የተፈረመውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት (Pretoria Agreement) በማፍረስ ወደ ቀድሞው አቋም ለመመለስ መወሰኑ ተገልጿል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ክልሉን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ በማዕከላዊ ኮሚቴው ሀሳብ ቀርቧል።

ውሳኔው በክልሉ ውስጥ ያለውን የውስጥ ክፍፍል ሊያባብስ እንደሚችል እና ከፌዴራል መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ ከፋ ግጭት ሊመልሰው እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: