የአርቴታ እና የተኩላዎቹ ጉዳይ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የመድፈኞቹ አለቃ ሚኬል አርቴታ ተጨዋቾቻቸው ሜዳ ላይ ያላቸውን ትኩረት እና ትብብር ለማሳደግ ልዩ በሆነ መንገድ አነሳስተዋል። አሰልጣኙ በቡድን ስብሰባ ወቅት የበርካታ ተኩላዎችን ምስል በመጠቀም ተጨዋቾቹ በምን አይነት ስሜት እና ጥንካሬ መጫወት እንዳለባቸው ትምህርት ሰጥተዋል።

ይህ የተኩላዎች ምስል በሜዳ ላይ “እንደ አንድ ልብ መምታት” እና “በጋራ ማደን” ያለውን ፋይዳ ለማሳየት የቀረበ ሲሆን፤ አርቴታ ተጨዋቾቹ እንደ ተኩላዎች ቁጡ፣ የማይበገሩ እና ለጋራ ግብ የሚፋለሙ እንዲሆኑ ይፈልጋል።

በተለይም በጨዋታ መሀል የሚፈጠሩ ፈተናዎችን በቡድን ጥንካሬ ለማለፍ እና ሁልጊዜም በሀይለኝነት ግባቸውን እንዲመቱ ለማድረግ ይህ የስነ-ልቦና ዝግጅት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ታምኖበታል። አርቴታ የዱር አራዊቱን የአደን ጥበብ ወደ እግር ኳስ ሜዳ በማምጣት መድፈኞቹን ለአሸናፊነት እያዘጋጁ ይገኛሉ።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#tikvah #Arsenal #MikelArteta #TheGunners #FootballNews


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2