የፋይናንስ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ ከፍተኛ የባንክ ባለሞያዎች ስለ ሚቶስ የ-AI ሞዴል ከፍተኛ ስጋት እንደገባቸው ገለጹየፋይ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የፋይናንስ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ ከፍተኛ የባንክ ባለሞያዎች ስለ ሚቶስ የ-AI ሞዴል ከፍተኛ ስጋት እንደገባቸው ገለጹ
የፋይናንስ ሚኒስትሮች፣ የልማት ባንክ ኃላፊዎች እና የፋይናንስ ባለሙያዎች የፋይናንስ ሥርዓቶችን ደህንነት ሊያናጋ ይችላል ተብሎ ስለታመነበት አዲስና ኃይለኛ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ከፍተኛ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
በአንትሮፒክ ኩባንያ የበለፀገው ‹‹ክላውድ ሚቶስ›› የተባለው ሞዴል በሁሉም ዋና ዋና የኮምፒውተር ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ድረ-ገጾች ላይ የደህንነት ክፍተቶችን ማግኘቱን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባዎች እንዲጠሩ ምክንያት ሆኗል።
ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ ሞዴሉ የሳይበር ደህንነት ድክመቶችን የመለየት እና እነዚሁኑ ተጠቅሞ ጥቃት የመሰንዘር ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ አቅም አለው።
የካናዳ የፋይናንስ ሚኒስትር ፍራንሷ-ፊሊፕ ሻምፓኝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ስብሰባ ላይ ስለ ሚቶስ ከባልደረቦቻቸው ጋር በሰፊው ተወያይተዋል።
ጉዳዩ በእርግጥም የሁሉንም የፋይናንስ ሚኒስትሮች ትኩረት የሚሻ እና አሳሳቢ ነው ያሉ ሲሆን፤ ‹‹ከሆርሙዝ ሰርጥ ጋር ያለው ልዩነት፣ እሱ የት እንደሚገኝና መጠኑ ምን ያህል እንደሆነ እናውቃለን ከአንትሮፒክ ጋር እየገጠመን ያለው ችግር ግን ‹‹ያልታወቀ እና እንግዳ›› መሆኑ ነው ብለዋል፡፡
የፋይናንስ ሥርዓታችንን የመቋቋም አቅም ለማረጋገጥ የጥንቃቄ እርምጃዎችና አሰራሮች እንዲኖሩን ከፍተኛ ትኩረት ይሻል በማለትም አክለዋል።Via.EthioFm
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2