የኢራን የበላይ መሪ በሕይወት ቢኖሩም “ቆስለዋል” ተባለአዲሱ የኢራን የበላይ መሪ አያቶላ ሞጅታባ ኻሜኒ በሕይወት ቢኖሩም “ቆስ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢራን የበላይ መሪ በሕይወት ቢኖሩም “ቆስለዋል” ተባለ
አዲሱ የኢራን የበላይ መሪ አያቶላ ሞጅታባ ኻሜኒ በሕይወት ቢኖሩም “ቆስለዋል እንዲሁም አካላቸው ተጎድቷል” ሲሉ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴዝ ስለ ኢራን ጦርነት ወቅታዊ መረጃ ሲሰጡ ተናግረዋል።
የቀድሞው የበላይ መሪ የአያቶላ አሊ ኻሜኒ ልጅ ሞጅታባ ኻሜኒ፥ከኢራን ጋር ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት በሆነው የመጀመሪያው የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መቁሰላቸው ተዘግቧል።
ይኸው ጥቃት አዛውንቱን ኻሜኒን የገደለ ሲሆን፥ የአዲሱን የበላይ መሪ ባለቤት እና በርካታ የቤተሰብ አባላትንም ሳይገድል እንዳልቀረ ይነገራል።
ሞጅታባ ኻሜኒ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በአደባባይ ያልታዩ ሲሆን፥ ስለ ጤና ሁኔታቸው የሚወጡ ዘገባዎችም የተለያዩ ናቸው።
ሄግሴዝ ስለ መሪው ሁኔታ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፥“አሁን ላይ ከእርሳቸው ብዙም የሚሰማ ነገር የለም ይህም የሚጠበቅ ነው። ከፍተኛ ፍርሃት አለ። በሕይወት እንዳሉ ቢታመንም፣ ቆስለዋል እንዲሁም አካላቸው ተጎድቷል። ሁኔታው ያው ነው” ብለዋል።
ሄግሴዝ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ እንደተናገሩት፥አዲሱ የኢራን የበላይ መሪ በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት በመፍራት፣ በመቁሰል እና በመሸሸግ ላይ እንደሚገኙ ገልጸው ነበር።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: