ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮፕ32 የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ገመገሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

ኢትዮጵያ የኮፕ32 ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ፣ ዝግጅቷን በላቀ ምልከታ ለመምራት ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም የጀመረቻቸውን ተግባራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መገምገማቸውን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በነበራቸው ስብሰባ፤ እስካሁን በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም ክፍተቶችን የመለየት እና ጥረቶቹ ከሀገራዊ ርዕይ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን የተዳሰሰበት መድረክ መካሄዱን ገልጸዋል።

ሂደቱን በግልጽ ግብ ለመምራት ቁልፍ አመራር መመደቡን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የኮፕ ፕሬዝደንት መዋቅርም የተቀናጀና የላቀ ውጤት የሚያስገኙ የቅድሚያ ተግባራቱን መጀመሩን ጠቁመዋል።

በመድረኩ ከግምገማ ባሻገር የጋራ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠንበታል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ትኩረታችን ግልጽ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በጠንካራ ትብብር፣ በተዋሃደ ታላቅ ርዕይ እና የጋራ ጽኑ ትጋት ተናበን ይህን ዓለም አቀፍ ሁነት በልህቀት በማስተናገድ የሀገርን ታላቅነት ዳግም ማሳየት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

EBC






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2