ፌስታልለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግሉ የፕላስቲኮች ምርቶችን በልዩ ሁኔታ ለመፍቀድ የልየታ መረጃ እየተሰበሰበ እንደሆነ ተገለጸ።ኢ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ፌስታል‼️
ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግሉ የፕላስቲኮች ምርቶችን በልዩ ሁኔታ ለመፍቀድ የልየታ መረጃ እየተሰበሰበ እንደሆነ ተገለጸ።
ኢትዮጵያ በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገችውን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ተከትሎ፣ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከለከሉ የአንድ ጊዜ ብቻ አገልግለው ከሚጣሉ የፕላስቲክ ምርቶች መካከል በልዩ ሁኔታ መፈቀድ ያለባቸውን ለመለየት መረጃዎች እየተሰበሰቡ እንደሆነ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለአሐዱ አስታውቋል።
ባለስልጣኑ አዋጁን ለማስፈጸም የሚያግዝ መመሪያ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የከተማ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ክትትል ዴስክ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ዓለሙ፣ “ተቋማት በልዩ ሁኔታ እንዲፈቀዱላቸው የሚፈልጓቸውን የፕላስቲክ ምርቶች ለይተው እንዲያቀርቡ የጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸዋል” ብለዋል።
በዚህ ሂደት በሱፐርማርኬቶችና በመገበያያ ስፍራዎች ሕብረተሰቡ እየተጠቀመባቸው የሚገኙ ምርቶች በአዋጁ አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 6 ላይ በተቀመጠው ድንጋጌ መሠረት፣ ይህ ልዩ ሁኔታ የፕላስቲክ ከረጢቶችን እንደማይመለከት ተገልጿል።
የፕላስቲክ ከረጢቶችን በልዩ ሁኔታ ማስገባትም ሆነ መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን፣ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ ምርቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ በአስተዳደራዊ ውሳኔ የሚቋጭ ቢሆንም የፕላስቲክ ከረጢቶችን ማምረት፣ መጠቀም፣ መሸጥ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እና ማከማቸት የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ኃላፊው አጽንኦት ሰጥተውበታል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2