“ሥራ የሚገኘው በዘመድና በዘር መሆኑን አውቃችሁ ተንቀሳቀሱ” — ዶክተር አረጋ ይርዳው
የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው፣ ተማሪዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመርቀው ወደ ሥራው ዓለም ሲሰማሩ ያለው ነባራዊ ሁኔታ “በዘመድ፣ በፓርቲ አሠራር እና በዘር” ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተረድተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ማቅረባቸውን ኖር ሬድዮ በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ ከተገኙ እንግዶች ሰምቷል።
ዶክተር አረጋ ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የ44ኛው ዙር ተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
ፕሬዚዳንቱ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት የሥራ ዓለም መመሪያ ላይ በሀገሪቱ ያለውን የሥራ ቅጥር ሁኔታ በግልጽ እንደሚከተለው ገልጸውታል፦”ተመርቃችሁ ስትወጡ ሥራ የሚገኘው በዘመድ፣ በፓርቲ አሠራር፣ በዘር እና በጐጥ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ መልኩ እንድትንቀሳቀሱ እንደሚያስፈልግ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ” ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ንግግር ያደረጉት ተመራቂዎች ከዩኒቨርሲቲ መውጣታቸውን ተከትሎ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ተጨባጭ ፈተና ለማሳወቅና አስቀድመው እንዲዘጋጁበት ለማሳሰቢያ እንደሆነ ተመልክቷል።
በብቃትና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አሠራር እንዲኖር በሚወተወትበት በዚህ ወቅት፣ እንዲህ ዓይነት ነባራዊ እውነታን የጠቆመ ንግግር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም መሪ መሰማቱ ልዩ ትኩረትን ስቧል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.