“በቃ ማለት በቃ ነው” — ትራምፕ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ ጥቃት በአስቸኳይ እንድታቆም ዋሽንግተን በንቃት እየከለከለች መሆኑን በይፋ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ በሊባኖስ እና በእስራኤል መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ተከትሎ ነው ይህንን መግለጫ የሰጡት።

ትራምፕ በራሳቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ በሆነው ትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ባስተላለፉት መልዕክት እስራኤል ከእንግዲህ ሊባኖስን እንደማትደበድብና ይህን እንዳታደርግም በዩናይትድ ስቴትስ መታገዷን በግልጽ አስፍረዋል። “በቃ ማለት በቃ ነው” ሲሉም ዩናይትድ ስቴትስ ግጭቱን ለማቆም ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሊባኖስ ለ10 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት በቴል አቪቭ እና ቤሩት ሰዓት አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን አዝዘዋል።

አክለውም ይህ የሊባኖስ እና እስራኤል ስምምነት አሜሪካ ከኢራን ጋር ከምታደርገው ቀጣይ ድርድር የተለየ መሆኑን አስገንዝበዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከሊባኖስ መንግስት ጋር በቅርበት መስራቷን እንደምትቀጥልና ከሂዝቦላ ጋር ያለውን ሁኔታ ለመፍታትም በትኩረት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።

ይህ የትራምፕ እርምጃ በመካከለኛው ምስራቅ ለወራት የቀጠለውን ደም አፋሳሽ ውጥረት ለማርገብ እና አዲስ የሰላም ምዕራፍ ለመክፈት የተወሰደ ወሳኝ ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#መናኸሪያfm #ሰበርዜና #ሊባኖስ #እስራኤል #ትራምፕ #መካከለኛውምስራቅ #አማርኛ #ዜና #ሰላም


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1