የቡና ገበያ ቀዝቅዟል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ላይ ተከስቶ የነበረው የዋጋ ንረት፣ በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ የታየው መረጋጋትና የተሻለ የምርት ትንበያ ተከትሎ ጉልህ ቅናሽ ማሳየቱ ተሰምቷል። በተለይም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ምክንያት ታንቆ የነበረው የንግድ መስመር ዳግም መከፈቱ ለዚህ ለውጥ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል

​ለረጅም ጊዜ የዓለምን ንግድ ስጋት ላይ ጥሎ የነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት በመርገቡ፣ የቡና ንግድ ፍሰት ወደ ቀድሞ ሁኔታው መመለስ ጀምሯል።

የኢራን መንግስት ስትራቴጂካዊ የሆነውን ይህን የንግድ መስመር ለጭነት መርከቦች ክፍት ማድረጉ፣ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረውን “መቼ ይደርስልናል?” የሚል ስጋት ቀርፎታል።

​የዓለማችን ግዙፍ የቡና አምራች ሀገራት ያሳዩት አፈጻጸምና ትንበያ ገበያውን በአቅርቦት እንዲጥለቀለቅ አድርገውታል።

​ብራዚል፦ በ2026/27 የምርት ዘመን እስከ 75.9 ሚሊዮን ከረጢት ከፍተኛ ምርት ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል።

​ቪየትናም፦ የሮቡስታ ቡና ላኪዋ ቪየትናም የወጪ ንግዷን በ14% ማሳደጓ ለዋጋው መውረድ ተጨማሪ ግፊት ሆኗል።

​በ2026 ዓ.ም የዓለም የቡና ትርፍ ምርት 10 ሚሊዮን ከረጢት ይደርሳል ተብሎ ይገመታል።

​ባለፈው ሳምንት ብቻ የአረቢካ እና የሮቡስታ ቡና ዋጋዎች የሚከተለውን የቅናሽ መጠን አሳይተዋል፦
​አረቢካ ቡና፦ በ2.28% ቅናሽ (ሳምንታዊ ዝቅተኛ ዋጋ)።

​ሮቡስታ ቡና፦ በ2.50% ቅናሽ።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#capitalnews ​#የቡናገበያ #ኢኮኖሚ #የዓለምዜና #ቡና #CoffeeMarket #GlobalEconomy #BrazilCoffee


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2