#Ethiopia | አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ፣ “ሰዎች ወደ ሕይወቴ ከገቡ በኋላ ደስ የማያሰኝ ባህሪይ እያሳዩኝና በጣም የሚጎዳኝን ተግባር እያደረጉብኝ እንኳን ዝም ብሎ የመታገስ ነገር ይታይብኛል”፡፡
እንደዚህ አይነት ሰዎች ካለልክ የመታገሳቸውና ሰዎቹ እንደፈለጉ የመሆናቸው ሁኔታ ትክክል እንዳልሆነ ቢያውቁትም፣ ምንም ነገር ባለማድረግ ሲጎዱ ይታወቃቸዋል፡፡
ከዚህ በታች ለዚህ አይነቱ ዝንባሌ አጋልጦ የሚሰጡንን የመነሻ ችግሮች ከነመፍትሄያቸው አቀርባለሁ፡፡
1. ሰዎችን የማጣት ወይም ሊከሰት የሚችለውን የማይያታወቅ ሁኔታ መፍራት
የችግራችን መነሻ ይህ እንደሆነ ካሰብን፣ የሰዎች ሁኔታው በማይመቸን ጊዜ ትክክለኛውን የእርምት እርምጃ ብንወስድ ከሚደርስብን ችግር የበለጠ ሁኔታውን በመታገሳችን እንደሚደርስብን ራሳችንን በማሳመን ተገቢውን ገደብ በማስቀመጥ የሚመጣውን መጋፈጥ የግድ ነው፡፡
2. በቀላሉ የስሜት ትስስር ውስጥ የመግባት ዝንባሌ
የችግራችን መነሻ ይህ እንደሆነ ካሰብን፣ ከሰዎች ጋር ስንላመድ በሁኔታው ውስጥ የምናገኘውን ምቹ ስሜት ለማጣት አለመፈለግ ሊያጠቃን ቢችልም እስከምንጎዳ ግን መድረስ ግን የለብንም፡፡ የስሜት ትስስር፣ እስራት ደረጃ መድረሱን እንዳወቅን መቁረጥ አለብን፡፡
3. ሰዎችን የመርዳት፣ ሁኔታቸውን understand የማድረግና ለእነሱ የማዘን ሁኔታ
የችግራችን መነሻ ይህ እንደሆነ ካሰብን፣ ሰዎችን መገንዘብና ለእነሱ ማዘን፣ አስቸጋሪና ጎጂ ባህሪያቸውን ካለአግባብ መታገስ ማለት እንዳልሆነ በማሰብ የቀይ መስመር ማስፈር አስፈላጊ ነው፡፡
4. ዝቅ ያለ የራስ በራስ ግምት እንዲኖረን ያደረገን አስተዳደግ
የችግራችን መነሻ ይህ እንደሆነ ካሰብን፣ የቀይ መስመራችን ሳይከበርና ተገፍተን ካደግን ለዚህ አይነት ልምምድ እንደሚያጋልጠን እውታውን በመጋፈጥ የግል ቀይ መስመር የማድረግን ልምምድ ቀስ በቀስ ማዳር አስፈላጊ ነው፡፡
5. ሰዎቹ እንደሚለወጡ ተስፋ ማድረግ
የችግራችን መነሻ ይህ እንደሆነ ካሰብን፣ ካለን ቅንነትና ከመንፈሳዊ አስተምህሯችን የተነሳ ሰዎች እንደሚለወጡ ብናምንም ሁኔታው ገደብ ሊይዝ እንደሚገባው በማሰብ፣ ሰዎች የራሳቸውን ሸክም እንዲሸከሙ መፍቀድ ተገቢ የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ መገንዘብ የግድ ነው፡፡
Dr eyob
Source: GetuTemesgen









No comments yet.