ውጭ ምንዛሪ የሚያድኑ የሴራሚክ ምርቶች በቅርቡ ለገበያ ይቀርባሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

ይህ የተገለፀው ኢትዮደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ”Golden Tier Level” የምርት አከፋፋይነት ደረጃ ከባይጃይ ሴራሚክ ማምረቻ ኢንዱስትሪ (ቱለፋ ሴራሚክ) የካቲት 27፣ 2018 ዓ.ም. ጋር ያደረጉትን የሴራሚክ ውጤቶችን የማከፋፈል ስምምነት ምክንያት በማድረግ በተካሄደ የማብሰሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ነው።

ሥነ ሥርዓቱ ታላላቅ እንግዶች በታደሙበት ሚያዝያ 10 2018 ዓ.ም በሎፍት አፓርትመንት ሆቴል ተካሂዷል። የሁለቱ ድርጅቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በተገኙበት የማብሰሪያ ሥነ-ሥርዓቱ የተካሄደ ሲሆን የተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎችም ንግግር አድርገዋል።

በማብሰሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተገለፀው የኢትዮጵያን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ለማገዝ እንዲሁም ጥራት ያላቸውን የቤት ውስጥ ማጠናቀቂያ ምርቶች ለደንበኞች በተሻለ ተደራሽነት ለማቅረብ ስምምነቱ አይንከፋች ይሆናል ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት የግንባታ ሥራዎች በአገሪቱ እየተስፋፉ መምጣታቸውን በዕለቱ የተገለፀ ሲሆን መንግሥትም ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት በተለይ በአገር ውስጥ የሚመረቱ እቃዎችን ለደንበኞች በማቅረብ የውጭ ምንዛሪን ማዳን ሁነኛ አማራጭ መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ጥራት የሚመረቱ የባይጃይ ሴራሚክ ውጤቶች( ቱለፋ ሴራሚክስ) በኢትዮደር ሰፊ የማከፋፈል መረብ አማካይነት ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ ያለመ መሆኑም በተሰጠው መግለጫ ተጠቅሷል።

ይህ በጋራ የተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት የሀገር ውስጥ ምርትን የማበረታታት፣ የውጭ ምንዛሬን በመቆጠብ እና ለኮንስትራክሽን ግብዓቶች የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ተገልጿል።

በዕለቱም ከመጀመሪያዎቹ የምርቱ ተጠቃሚ የኮንስትራክሽን ፕሮጄክት ባለቤቶች ጋር እና ቀዳሚ ሁለተኛ ደረጃ አከፋፋዮች ጋር የመግባቢያ ሠነዶች ተፈርመዋል።

የማብሰሪያ ሥነ -ሥርዓቱ ላይ እንደተወሳው ለኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሆኑ ግብአቶችን አገር ውስጥ አምርቶ አገር ውስጥ በመሸጥ በየጊዜው እያደገ ለመጣው የአገሪቱ የግንባታ ሥራ ትልቅ ክፍተት እንደሚሞላ ተነግሯል።

ከአዲስ አበባ በ65 ኪ.ሜ ርቀት በሚገኝ ቱለፋ በተባለ ቦታ የሚገኘው የባይጂያ ፋብሪካ፣ ከ50 ሚሊዮን ዶላር በሚበልጥ ኢንቨስትመንት የተገነባ ሲሆን፣ በዓመት 14 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የሚሸፍኑ የሴራሚክ ምርቶችን የማምረት አቅም አለው።

ይህም ፋብሪካውን በኢትዮጵያ ግዙፉ የሴራሚክ አምራች ድርጅት ያደርገዋል።
ፋብሪካው ሥራውን ሲጀምር የኢትዮጵያን ዓመታዊ የሴራሚክ ምርት ፍላጎት 20 በመቶ መሸፈን የሚችል ሲሆን፤ በሙሉ መንቀሳቀስ ሲጀምር ደግሞ እስከ 70 በመቶ የምርት ፍላጎትን ያሟላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም የሴራሚክ ምርትን ከውጭ ሀገራት ለማስገባት የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በእጅጉ ያስቀራል።

ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ ሐሳብ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ለማስፋፋት ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
የባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ተወካይ በበኩላቸው ፣ይህ ትብብር በኢትዮጵያ እያደገ ያለውን ፍላጎት ማሟላት የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለማቅረብ ጠንካራ መሠረት እንደሚጥል ገልጸዋል።

የኢትዮደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ በላይ እንዳሉት በዕለቱ የተደረገው የማብሰሪያ ሥነ ሥርዓት ጥራት ያለው የአገር ውስጥ ምርትን ወደ ገበያ ለማምጣት ሥራ የጀመርንበት ትልቅ ነው ብለዋል። የባይጃይ ሴራሚክ ፋብሪካ የሥራ መሪ ሚስተር ሳም በበኩላቸው ፋብሪካው ከ 2 ሳምንት በኃላ ማምረት ሲጀምር ደንበኞች ተገቢውን ምርት እንደሚያገኙ አንጠራጠርም ብለዋል።

ኢትዮደር ኃ.የተ.የግ.ማ በኢትዮጵያ ውስጥ የአሜሪካውን የኮህለር የመታጠቢያ ቤት እቃዎች እና የሰርቢያውን የፔሽታን Pipe ላለፉት 7 ዓመታት ብቸኛ ወኪል እና አከፋፋይ በመሆን ለሀገር ውስጥ ሲያቀርብ የቆየ ነው።

በሎጂስቲክስ ዘርፍ በኢትዮጵያ በማዕድን ነዳጅ እርሻ እና ሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ የውጭ ኩባንያዎችን ሥራቸውን ያለሀሳብ እንዲከውኑ ማንኛውንም የሎጂስቲክ አገልግሎት በመስጠት የካበተ ልምድ አለው።

ኢትዮደር ኃ.የተ.የግ.ማ. ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ የኃይል እና ዘላቂ ትራንስፖርት የምታደርገውን ሽግግር በመደገፍ ለኢትዮጵያ መንገዶች ተስማሚ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን በማምጣት እየሠራ ይገኛል።

የሁነቱ እና የሚድያ ማስተባበሩ ተግባር በተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን (ዕዝራ እጅጉ) እንደተዘጋጀም ለማወቅ ተችሏል






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2