#Ethiopia | የማንችስተር ሲቲው ስትራቴጂስት ፔፕ ጋርዲዮላ አርሰናልን መግጠም ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነና መድፈኞቹ አሁንም ለዋንጫው ያላቸውን የበላይነት ገለጹ። ጋርዲዮላ የአርሰናልን ወቅታዊ ጥንካሬ ሲያደንቁ “አሁንም ቢሆን የሊጉ መሪ አርሰናል ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
የመድፈኞቹን የኋላ ክፍል ጥንካሬ በተመለከተም ጋርዲዮላ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፦
”ከጋብሬል እና ሳሊባ ጋር መፋለም እጅግ ከባድ ነገር ነው። እውነት ለመናገር በሃላንድ ቦታ ሆኜ ከእነሱ ጋር ከመታገል ይልቅ ቁጭ ብዬ መጽሐፍ ማንበብን እመርጣለሁ።”
አሰልጣኙ አክለውም አርሰናል እጅግ ድንቅ ቡድን እንደሆነና እነሱን መግጠም አድካሚ መሆኑን ጠቁመው፣ ምንም እንኳን መድፈኞቹ በግብ ክፍያም ሆነ በነጥብ መሪነቱን ቢይዙም ሲቲዎች አሁንም ለዋንጫው ያላቸው ተስፋ እንዳልተሟጠጠ ገልጸዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#Arsenal #ManCity #PepGuardiola #PremierLeague #Saliba #Gabriel #Haaland #FootballNews #EPL
Source: GetuTemesgen









No comments yet.