የጻድቁ አቡነ አረጋዊ ረድኤት እና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት፡፡

አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ናቸው፡፡ ዘጠኙ ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ሲሆን ተወልደው ያደጉት በአንድ የሮም ግዛት ሥር በተለያየ ቦታ ነው፡፡ አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚገባ ያጠኑት እነዚህ አበው ሰማያዊውን ክብር መርጠው ክርስቲያኖች በሚሳደዱበት በ5ኛው ክፍለ ዘመን በቅድሚያ አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ከዚያም ሌሎቹ ከሮም ወደ ግብጽ በርሃዎች፣ በ470ዎቹ ዓ.ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ በአረጋዊ መሪነት ወደ ኢትዮጵያ በምናኔ መጥተዋል፡፡

ንጉሡም በመልካም ተቀብሎ በአክሱም ቤተ ቀጢን ማረፊያ ቦታ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም የግዕዝ ቋንቋ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ በአቡነ ሰላማ፣ በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለውንና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ የነበረውን ክርስትና እንደገና አቀጣጠሉት፤ ለዓመታትም ወንጌልን ሰበኩ በርካታ መጻሕፍትንም ተረጎሙ፡፡ በኋላም የየራሳቸው የምናኔ ቦታ በመምረጥ ወንጌልን እየሰበኩና ስለሀገራችን እየጸለዩ ኖረዋል፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊ በደብረ ዳሞ ታላቅ ገድል ፈጽመዋል፡፡ ማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ፡፡ ጻድቁ ተጋድሏቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል፡፡

ጌታም የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ጥር 14ም ጻድቁ የተወለዱበት ቀን ነው፡፡

መናንያንና ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ የወንጌል ብርሃን እንዲበራ፣ ትልቅ ሥራ ሰርተዋል፡፡ ጸሎታቸው አሁንም ተአምር ያደርጋል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: