ጦርነቱ በነዳጅ ብቻ ሳይሆን በኮንዶም ዋጋ ላይ ጭምር ተጽኖ አሳድሯል ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በዓለማችን ግዙፉ የኮንዶም አምራች የሆነው የማሌዥያው ካሬክስ (Karex) ኩባንያ፣ በኢራን ጦርነት ሳቢያ እያጋጠመው ባለው የጥሬ ዕቃ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት የምርት ዋጋን ለመጨመር እየተገደደ መሆኑን አስታውቋል።

​የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጎህ ሚያ ኪያት ለሮይተርስ እንደገለጹት፣ የጦርነቱ መፋፋም በተለይም በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ በማስተጓጎሉ፣ ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ከ20% እስከ 30% የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ ሊደረግ ይችላል።

​ዋነኛ ምክንያቶች፡

​-ከየካቲት ወር ጀምሮ በቀጠለው ጦርነት ምክንያት ለምርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እጥረት አጋጥሟል።

-ምርቶች በባህር ላይ ለረጅም ጊዜ ተከማችተው መቆየታቸውና የትራንስፖርት መስመሮች መለዋወጥ ወጪውን አናርቶታል።

_ለማሸጊያና ለምርት ሂደት የሚወጡ ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል።

​መቀመጫውን ማሌዥያ ያደረገው ይህ ግዙፍ ኩባንያ፤ ONE, Trustex, Carex እና Pasante የተሰኙ ታዋቂ የኮንዶም ብራንዶችን የሚያመርት ሲሆን፣ በዓመት ከ5 ቢሊዮን በላይ ኮንዶሞችን ለዓለም ገበያ ያቀርባል።
​ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ለጥቂት ወራት የሚበቃ ክምችት ቢኖረውም፣ ጦርነቱ በዚህ መልኩ የሚቀጥል ከሆነ ግን የዋጋ ጭማሪው የማይቀር መሆኑን ስራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#Karex #GlobalEconomy #IranWar #SupplyChain #BusinessNews #CondomPrice #SafeSex #Ethiopia #newsupdate


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1