#Ethiopia | ደቡብ ሱዳን በታሪክ አጋጣሚዎችና በፖለቲካዊ ውጥረቶች መካከል ሆና፣ ለዓመታት የተራዘመውን ብሔራዊ ምርጫ በመጪው ታህሳስ ወር ለማካሄድ እየተሰናዳች ነው። ሀገሪቱ በርስ በርስ ጦርነት አፋፍ ላይ ባለችበት በዚህ ወቅት ምርጫ ለማካሄድ መታቀዱ፣ ለብዙዎች “በእሳት ላይ የመጫወት” ያህል አስፈሪ ሆኖባቸዋል።
በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሚመሩ የመንግስት ኃይሎች እና ከምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ባላቸው ቡድኖች መካከል ያለው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ባለሙያዎች ሁኔታው ካልረገበ ሀገሪቱ ወደ ቀድሞው አስከፊ የርስ በርስ ጦርነት ልትመለስ እንደምትችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ግጭቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ያፈናቀለ ሲሆን፣ ለተረጂዎች ደራሽ የሆኑ የእርዳታ ድርጅቶችም የጥቃት ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ።
እ.ኤ.አ በ2018 በተደረገው የሰላም ስምምነት መሠረት ምርጫው በ2022 መካሄድ ነበረበት። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ሲራዘም ቆይቶ አሁን “የመጨረሻ” ወደ ተባለለት የጊዜ ሰሌዳ ተደርሷል።
ምንም እንኳን የሀገሪቱ የኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ምርጫው መካሄድ አለበት ብለው በአቋማቸው ቢጸኑም፣ በመሬት ላይ ያሉ እውነታዎች ግን ሌላ ታሪክ ይናገራሉ።
በሰላም ስምምነቱ የተቀመጠው የተፋላሚ ኃይሎችን የማዋሃድ ሂደት እስካሁን ፍሬ አላፈራም።
ሀገሪቱ በከፍተኛ ሙስና እና በከፋ ድህነት ውስጥ እየማቀቀች ትገኛለች።
ሂደቱ ከተሳካ፣ ደቡብ ሱዳን ነፃነቷን ካገኘች ከ15 ዓመታት ወዲህ የምታካሂደው የመጀመሪያው ብሔራዊ ምርጫ ይሆናል።
ደቡብ ሱዳን በታህሳስ ወር ወደ ምርጫ ጣቢያ ታመራ ይሆን ወይስ የጠመንጃ ድምፅ የድምፅ መስጫ ሳጥኖቹን ያሸንፋቸዋል? የሚለውን ጊዜ የሚመልሰው ይሆናል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#SouthSudan #SudanNews #Election2024 #EastAfrica #PeaceAndConflict #SalvaKiir #RiekMachar #ደቡብ_ሱዳን
Source: GetuTemesgen









No comments yet.