#Ethiopia | በዓለማችን ግዙፉ የኮንዶም አምራች የሆነው የማሌዥያው ካሬክስ (Karex) ኩባንያ፣ በኢራን ጦርነት ሳቢያ እያጋጠመው ባለው የጥሬ ዕቃ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት የምርት ዋጋን ለመጨመር እየተገደደ መሆኑን አስታውቋል።
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጎህ ሚያ ኪያት ለሮይተርስ እንደገለጹት፣ የጦርነቱ መፋፋም በተለይም በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ በማስተጓጎሉ፣ ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ከ20% እስከ 30% የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ ሊደረግ ይችላል።
ዋነኛ ምክንያቶች፡
-ከየካቲት ወር ጀምሮ በቀጠለው ጦርነት ምክንያት ለምርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እጥረት አጋጥሟል።
-ምርቶች በባህር ላይ ለረጅም ጊዜ ተከማችተው መቆየታቸውና የትራንስፖርት መስመሮች መለዋወጥ ወጪውን አናርቶታል።
_ለማሸጊያና ለምርት ሂደት የሚወጡ ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል።
መቀመጫውን ማሌዥያ ያደረገው ይህ ግዙፍ ኩባንያ፤ ONE, Trustex, Carex እና Pasante የተሰኙ ታዋቂ የኮንዶም ብራንዶችን የሚያመርት ሲሆን፣ በዓመት ከ5 ቢሊዮን በላይ ኮንዶሞችን ለዓለም ገበያ ያቀርባል።
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ለጥቂት ወራት የሚበቃ ክምችት ቢኖረውም፣ ጦርነቱ በዚህ መልኩ የሚቀጥል ከሆነ ግን የዋጋ ጭማሪው የማይቀር መሆኑን ስራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#Karex #GlobalEconomy #IranWar #SupplyChain #BusinessNews #CondomPrice #SafeSex #Ethiopia #newsupdate
Source: GetuTemesgen









No comments yet.