ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በኦሮሚያ ክልል የ4.5 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።
ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን እና አጣዳፊ የምግብ እጥረት ችግሮችን ለመከላከል የሚያስችል የ4.5 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
የድርጅቱ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንበሱ ቶላ እንዳሉት ይህ ባለብዙ ዘርፍ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጀክት በጤና፣ በሥርዓተ-ምግብ እና በንፁህ መጠጥ ውሃ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው።
ፕሮጀክቱ 4.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት የተመደበለት ሲሆን ለዚህም በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፈው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ፈንድ (EHF) ድጋፍ አድርጓል።
የፕሮጀክቱ ዋና ግብ በኦሮሚያ ክልል 5 ዞኖች በተመረጡ 7 ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ 295 ሺህ ገደማ የሚሆኑ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን፤ በችግር ምክንያት የሚከሰቱ የህመም እና የሞት መጠኖችን ፈጣን እና የተቀናጀ ምላሽ በመስጠት መቀነስ ነው።
ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ከ24 ዓመታት በላይ ለተቸገሩ ወገኖች የደረሰ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን፤ የዛሬውን ከ295 ሺህ በላይ ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ ያደረገው 17ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን እያደረገ ባለበት ወቅት ነው።



Source: FastMereja









No comments yet.