በአንድ የእንግዳ ማረፊያ ቤት በተደረገ ብርበራ በርካታ ህገ ወጥ መድኃኒቶች ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ።

- Advertisement -
Sidebar AD

ዮሴፍ ኩራባቸው እና ዮሐንስ የስጋት የተባሉ ተጠርጣሪዎች ምንም ዓይነት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው በህገ ወጥ መንገድ በርካታ መድኃኒቶችን አከማችተው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ያማዝ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት የእንግዳ ማረፊያ 3ኛ ፎቅ ከቀኑ 7:30 ላይ ነው ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የህብረተሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ህግን በተከተለ መንገድ ባደረገው ብርበራ ጠቅላላ የዋጋ ግምታቸው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያውጡ ለኩላሊትና ለካንሰር ህመምተኞች የሚሰጡ በርካታ መድኃኒቶች፣ መርፌዎችና የህክምና ቁሳቁሶች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ከአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

ህብረተሰቡ ትክክለኛነታቸውና ንጽህናቸው በህክምና ባለሙያዎች ያልተረጋገጡ መድኃኒቶችን ከመግዛት እራሱን መቆጠብ እንዳለበት የተገለፀ ሲሆን ያለ ምንም የንግድ ፈቃድ የሚሸጡና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል ሁሉም ለፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።

Addis Ababa police






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1