ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው ተሾሙጠቅላይ ሚኒ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው ተሾሙ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአኅጉር ደረጃ ዘርፉን እንዲመሩ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ሹመቱን እንደሰጣቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ በዘርፉ እያሳየች ያለው ተሞክሮ እውቅና ማግኘቱ፣ በሀገሪቱ የተቋቋመው የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ኢንስቲትዩት እና የተቀረጸው ብሔራዊ ስትራቴጂ ውጤታማነት ተመራጭ እንዳደረጋቸው ፅ/ቤታቸው የሹመት ደብዳቤውን ጠቅሶ ገልጿል፡፡
አኅጉራዊው ሹመት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ነፃነት እና በክህሎት ልማት የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለአፍሪካ አህጉር ተሞክሮ እንዲሆን ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርም ተመላክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው የካቲት ወር የኅብረቱ የሰው ሠራሽ አስተውህሎትና ዲጂታል ጤና አምባሳደር ሆነው መሾማችው ይታወሳል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2