ሜታ በ’AI ሰበብ ሰራተኞቹን ሊያሰናብት ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ ባለቤት የሆነው ሜታ ኩባንያ በዓለማቀፍ ደረጃ 10 በመቶ የሚሆኑ ሰራተኞቹን ለመቀነስ መወሰኑ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

​ኩባንያው በዓለም ዙሪያ ካሉ ሰራተኞቹ መካከል 10 በመቶ የሚሆኑትን ለማሰናበት ወስኗል።

​ሜታ በ8,000 በሚሆኑ የተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ አዲስ ቅጥር ለማቆም እና ያሉትንም ለመቀነስ አቅዷል።

​ይህ ውሳኔ በተለይ በአየርላንድ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የስራ አጥነት ስጋት እንዲያንዣብብ አድርጓል።

​ሜታ ይህንን መጠነ ሰፊ የሰው ኃይል ቅነሳ ለማድረግ የፈለገው፣ ነባር የስራ ዘርፎችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ለመተካት ባለው እቅድ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል። ይህም ኩባንያው ወደፊት ስራዎቹን ይበልጥ በቴክኖሎጂ የታገዙ ለማድረግ የጀመረው ሽግግር አካል ተደርጎ ተወስዷል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#Meta #AI #TechNews #BusinessPost #IrelandTech #JobMarket


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: