#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ የሚገኙ ዘላቂ ማረፊያዎችን (መካነ መቃብሮችን) ከቀብር አገልግሎት ባለፈ ለህዝብ ክፍት የሆኑ የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎች ለማድረግ የመልሶ ማልማት ስራ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።
የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ እንደታወቀው፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ መካነ መቃብርን ጨምሮ በርካታ ማረፊያዎች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል። በዚህም የመካነ መቃብር ስፍራዎች የነበራቸው “የፍርሃት ቀጠና” ገጽታ ተቀይሮ፣ ለከተማዋ ውበትና ለነዋሪው እረፍት እንዲሰጡ ታቅዷል።
የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እና የሌሊት መብራት ጌጥ ዝርጋታ። ለጎብኚዎች ምቹ የሆኑ የመቀመጫ ወንበሮች እና የንጽህና መጠበቂያዎች ግንባታ። ሰፊ የአረንጓዴ ስፍራዎች እና የቢሮ መሠረተ ልማቶች ማሟላት ስራዎች ተሰርቷል።
Source: FastMereja









No comments yet.