በኦቲዝም ጥላ ስር ላሉ ልጆች የሚሰጥ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በሻምፒዮንስ አካዳሚ ስለ ኦቲዝም ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለመስጠት አላማ ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል።

የሻምፒዮንስ አካዳሚ ባለቤትና የአዕምሮ ህክምና ባለሙያ የሆኑት ወይዘሮ መዓዛ መንክር በመርሐግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በህብረተሰቡ ውስጥ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች በስፋት እንደሚገኙ ገልጸው እነዚህ ልጆች እንደማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በእኩልነት መታየትና መስተናገድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

​ወይዘሮ መዓዛ አክለውም ለልዩ ፍላጎታቸው ትኩረት የሚሰጥና ሁሉንም የሚያካትት ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸው በተለይም የኦቲዝም ጉዳይ የብዙዎችን ትኩረት የሚሻ በመሆኑ ስለ ሁኔታው ግንዛቤ ማስጨበጥ ወሳኝ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።

በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ልጆች ተገቢውን ትምህርትና ድጋፍ ካገኙ የራሳቸውን አቅም ማሳደግና በህብረተሰቡ ውስጥ የራሳቸውን አዎንታዊ ሚና መጫወት የሚችሉ በመሆኑ ቤተሰቦች፣ ትምህርት ቤቶች፣ መንግስትና መላው ህብረተሰብ ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባም ባለሙያዋ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

​ሻምፒዮንስ አካዳሚ በኦቲዝም ጉዳይ ላይ ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ በርካታ ተማሪዎችን ተቀብሎ ከመደበኛ ተማሪዎች ጋር አካቶ በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን ተማሪዎቹም በሙያው በሰለጠኑ መምህራን እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ።

በአካዳሚው ውስጥ የሚሰጡ የድጋፍ አገልግሎቶችም ልጆቹ የንግግር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሚረዳ የስፒች ቴራፒን፣ ባህሪያቸውን ለማረጋጋት የሚረዳ የባህሪ ማረቅ ፕሮግራምን፣ እንዲሁም አካላዊ ቅንጅታቸውን ለማሻሻል የሚያስችላቸውን የኦኩፔሽናል ቴራፒ አገልግሎቶችን ያካተቱ ናቸው።

​ከዚህ በተጨማሪም ተማሪዎቹ በትምህርታቸው ከእኩዮቻቸው ጋር እኩል መጓዝ እንዲችሉ ፕሪ-አካዳሚክስ የተባለ ልዩ የማስተማርያ ዘዴ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1