ቱርክ ከአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ስምምነት በኋላ ሆርሙዝን ከፈንጂ ማጽዳት ላይ ልትሰማራ እንደምትችል ገለጸች

- Advertisement -
Sidebar AD

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን በቴህራን እና ዋሽንግተን ሊደረስ ከሚችል የሰላም ስምምነት በኋላ አገራቸው የሆርሙዝ ወሽመጥን ከፈንጂ የማጽዳት ሥራ ላይ መሳተፍ እንደምትችል አስታወቁ።
ፊዳን አርብ ምሽት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከማንኛውም ስምምነት በኋላ የቴክኒክ ቡድን በወሽመጡ የተጠመዱ ፈንጂዎችን ማምከን ሥራ ላይ ለመሠማራት እየጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል።

አክለውም ቱርክ እንዲህ ዓይነት ጥረቶችን እንደ ሰብዓዊ ግዴታ እንደምትመለከተው ገልጸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማንኛውም የፈንጂ የማምከን ሥራ የሚሠራው ከተለያዩ አገራት በተውጣጡ ቴክኒካል ቡድን መሆንን ገልጸው ከኢራን እና የአሜሪካ የሰላም ስምምነት በኋላ የሚመሠረት መሆኑን አስታውቀዋል።
ቱርክ በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ በፈንጂ ማምከን ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ረገድ “ችግር የለባትም” ብለዋል።
ፊዳን ወደፊት ከተለያዩ አገራት ተውጣጥቶ የሚመሰረተው የቴክኒክ ባለሙያዎች ጥምረት የአዲስ ግጭት አካል የሚሆን ከሆነ ቱርክ አቋሟን መልሳ እንደምትመለከት አስጠንቅቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፊዳን ከኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በፓኪስታን በሚደረገው ቀጣይ ዙር ውይይት ሊፈቱ ይችላሉ ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

BBC


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: