አልማዝ ዴንታል ላቦራቶሪ አዳዲስ የጥርስ ህክምና ቴክኖሎጂዎችን አስተዋወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

የ-አልማዝ ዴንታል ላቦራቶሪ ለሃገራችን ኢትዮጵያ ምርት አዲስ የሆኑ የጥርስ ህክምና ቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 18 2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በተደረገ መርሀ -ግብር አስተዋወቀ።

የ-አልማዝ ቢዝነስ ግሩፕ ንዑስ ክፍል የሆነው የ-አልማዝ የጥርስ ህክምና ላቦራቶሪ፣ በዛሬው እለት በነበረው ዝግጅቱ ላይ የላቀ የአርቴፊሻል ጥርስ መፍትሄ
ሔዎችን አዲስ ስብስብ ለማቅረብ መዘጋጀቱን በዕለቱ ለታደሙ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች አስረድቷል።

ይህ እርምጃ በጥርስ ህክምና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ውስጥ አዳዲስ ምርቶችን፣ በትክክለኛው እና ልህቀት በተሞላበት አግባብ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ እንደሚያሳይም በዕለቱ ተወስቷል።

የ-አልማዝ የአርቴፊሻል ጥርሶች አምራች ላቦራቶሪ በልህቀት ላይ የተመሠረተ አቀራረብን በመከተል፣ ከዘመናዊ የገበያ ፍላጎቶችና ከኢንዱስትሪ መመዘኛዎች ጋር የሚስማሙ መፍትሔዎችን ይዞ መቅረቡንም የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ያስረዳሉ።

በዕለቱ ይህንን በአገር ውስጥ የተመረተ አርቲፊሻል ጥርስ ገዝተው የተጠቀሙ የጥርስ ህክምና ባለቤቶች ምርቶቹ በጥራት የተሠሩ መሆኑን መስክረዋል። በዚህ ድርጅቱ ሙያዊ ሥራን ከወደፊት አስተሳሰብ ጋር በማጣመር ላይ የተመሠረተ መሆኑም ተገልጿል።

ኩባንያው ለደንበኞቹ የሚታወቅ እሴት መፍጠር ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት በአሁኑ ሰዓት አለም የደረሰበትን የጥርስ ህክምና ለአለም ለማስተዋወቅ እየሠራ እንደሚገኝም ተነግሯል።

የ-አልማዝ የአርቴፊሻል ጥርስ አምራች ላቦራቶሪ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የጥርስ ማከምያ ምርቶችን ሃገር ውስጥ ባቋቋመው የማምረቻ ድርጅት ውስጥን በማዘጋጀት ለተጠቃሚ በማቅረብ የታወቀ ሲሆን፣

* Zirconia
* Porcelain-Fused-to-Metal (PFM)
* Ceramic Restorations
* Veneers
* Retainers በተሰኙት መስኮችም ላይ አተኩሮ እየሠራ ይገኛል።

ላቦራቶሪው የቴክኒክ ክህሎትን ከዘመናዊ የምርት ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር የጥርስ ህክምና ባለሙያዎችን ተለዋዋጭ ፍላጎቶች በትክክል አሟልቶ በመስራት መርሆች በመነሳት አዳዲስ ጥራታቸውን የጠበቁ በዛው በላቦራቶሪው ውስጥ የሚመረቱ መፍትሔዎች ይዞ እንደመጣ በመግለጫው ላይ ተወስቷል።

ኩባንያው ከተጠቀሱት ምርቶች ባሻገር ገቢ ወጪ ጥርስን የማስተካከያ መሣሪያዎች (Flexible Dentures)
የህክምና መመሪያዎች (Surgical Guides)
Zirconia I-Bar
የጥርስ መዛነፍን የሚያስተካክሉ የህክምና ቁሶችን — Ye-Almaz Aligners ምርቶችን ይዞም መጥቷል።

እነዚህ መፍትሔዎች የታካሚዎችን ምቾት ለማሻሻል፣ የህክምና ትክክለኛነትን ለማሳደግ እና የክሊኒካል ውጤቶችን ለማበረታታት የተነደፉም ናቸው።

Ye-Almaz Aligner የጥርስ መዛነፍን የሚያስተካክሉ የህክምና ቁሶችን ለ ኦርቶዶንቲክ መፍትሔ የተገነባ ሲሆን፣ ከተለመደው የጥርስ ማሰሪያ ብሬሶች በተለየ ሁኔታ ቀለምም ሆነ የሚታይ ማሳሪያ ስለሌለው በሚለብስበት ጊዜ እጅግ የማይታይ እና ከፍተኛ ምቾት እንደሚሰጥም ታውቋል።

በምርት ማስተዋወቅ መርሀ ግብሩ ላይ በጥርስ ህክምና ሙያ ላይ የተሠማሩ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን በጥርስ ህክምና ሙያ አለምአቀፍ ሽልማት ያገኙት ህንዳዊው ዶክተር ኤም ኬም በቪድዮ የታገዘ ገለፃ ሰጥተዋል።

“ግባችን በቀጣይነት ለጥርስ ህክምና ደንበኞቻችን አስተማማኝና ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት ማቅረብ ሲሆን በቀጣይነት ክሊኒካዊ አፈፃፀምን እና የታካሚ ልምድን የሚያሻሽሉ መፍትሄዎች ይዞ ይመጣል ።

“ይህ ጅምር አቅማችንን ለማስፋት እና ለእድገታችን አስተዋፅዖ ለማድረግ በምናደርገው ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው::

በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን፣ አጋሮችን እና ደንበኞችን በአንድ ቦታ በማሰባሰብ አዳዲስ ፈጠራዎችን ለማስተዋወቅ እና በጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ማህበረሰብ ውስጥ አጋርነትን ለማጠናከር ይረዳል” ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይታይ ተስፋዬ ገልፀዋል።

የ-አልማዝ የሚለው ስያሜ ለመስራቾቹ እናት መታሰቢያ እንዲሆን በስማቸው የተሰየመ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2