‎የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምስጋና አቀረበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከትግራይ ክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ዋና ወንጀለኛ ይትባረክ ዳዊትን ከነግብረአበሮቹ በቁጥጥር ሥር በማዋሉ ለዚህ ቁርጠኛ ተግባር በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ምስጋናና አድናቆቱን ገልጿል።

‎ኤምባሲው በማህበራዊ የትስስር ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ ይትባረክ ዳዊት የተባለውን ግለሰብና አስር ተባባሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተከናወነው ኦፕሬሽን በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀለኞች ላይ የተመዘገበ ትልቅ ስኬት መሆኑን አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ወንጀለኞች ከ100 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ህይወት መጥፋትና በፈፀሙት የተለያዩ ኢሰብአዊ ድርጊቶች ተጠያቂ እንዲሆኑና ተጎጂዎች ፍትህ እንዲያገኙ ያስቻለ መሆኑን በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ አስፍሯል።

‎የኢትዮጵያ የፀጥታ ተቋማት ከዓለም አቀፍ አጋሮች እና The Regional Operational Centre in support of the Khartoum process (ROCK) ጋር በመተባበር የፈጸሙት ይህ ትልቅ ተግባር፥ ዓለም አቀፍ ትብብር ለውጤት እንደሚያበቃ ማሳያ መሆኑን ጠቁሟል።

‎ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልን ለመከላከልና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከሚደርሱባቸው እንግልትና ኢሰብአዊ ድርጊቶች ለመጠበቅ አሜሪካ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ አገሮቿ ጎን እንደምትቆም ኤምባሲው በመግለጫው አረጋግጦ በትብብር ከተሰራ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ማስቆም እንደሚቻል መልዕክቱን አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2