መረጃፌደራል ፖሊስ ከቴዲ አፍሮ ጋር በተያያዘ የተሰራጨው “የስቱዲዮ ዘረፋ” መረጃ መሠረተ ቢስ ነው ሲል  ገለጸበከያኒ ቴዎድሮስ…

- Advertisement -
Sidebar AD
መረጃ‼️
ፌደራል ፖሊስ ከቴዲ አፍሮ ጋር በተያያዘ የተሰራጨው “የስቱዲዮ ዘረፋ” መረጃ መሠረተ ቢስ ነው ሲል  ገለጸ
በከያኒ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የቅርብ ሰዎች ላይ ተደርጓል የተባለውን እስርና ክልከላ እንዲሁም የስቱዲዮ ዝርፊያ በተመለከተ ምላሽ የሰጡት የፌዴራል ፖሊስ ሃላፊው መረጃው መሠረተ ቢስና ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባበሉ።
የታዋቂው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ  ኢትዮሪካ የተሰኘ አልበሙን ለህዝብ ይፋ ካደረገ በኃላ በዙሪያው ያሉት ሰዎች ላይ እስር መፈጸሙ እንዲሁም “የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ አካላት የድምፃዊውን ስቲድዮ እቃዎች እና ለህዝብ ጀሮ ያልደረሱ ስራዎቹን ተዘርፈዋል” መባሉን ተከትሎ አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ከፌደራል ፖሊስ ምላሽ ጠይቃለች።
ፖሊስም “የፌዴራል ፖሊስ እንዲህ ዓይነት ወንጀል አይሰራም። ሰብዕናውም አይደለም” በማለት ለአዲስ ማለዳ ምላሹን ሰጥቷል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: