ተቆጣሽኝ በሚል አክስቱን የገደለው ግለሰብ የሞት ቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት።

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ክልል ልዩ ቦታው ኢካ ሳይት ብሎክ 705 የቤት ቁጥር 59 ውስጥ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 4 ሠዓት ነው ወንጀሉ የተፈፀመው።

በአካባቢው ላይ የሟች ማንነት የማይታወቅና የተወሰነ የሰው ቅሪት አካል በመገኘቱ ከአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ጥቆማ ይደርሳል። ፖሊስም የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ የሟችን ማንነት ለመለየት እና የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት ለመለየት በተደረገው ጥረት በሠዓታት ውስጥ ሟችን መለየት እና በወንጀሉ የተጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ሊያውል መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ም/ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።

ፖሊስም በተከሳሽ ሻምበል ሙሉጌታ ላይ በተደረገ ምርመራ ሟች ወርቅነሽ ኃይሌ የተባለችው የ36 ዓመት ጎልማሳ ስትሆን በጉምሩክ አስተላላፊነት የስራ መስክ ላይ እየሰራት የነበረች ስትሆን በተገለፀው አካባቢ መኖር ከጀመረች 4 ወራትን አስቆጥራለች።

ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ/ም የወንድሟ ልጅ የሆነውን ተከሳሽ ሻምበል ሙሉጌታ እሷ ጋር ተቀምጦ የቀን ስራ ለመስራት ከክፍለ ሀገር መምጣቱንና አብረው መኖር መጀመራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሰው መግደል ወንጀል ምርመራ መምሪያ ለማወቅ ችሏል።

መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሸቱ 12 ሰአት አካባቢ ስራ ውላ ወደ ቤቷ ገብታ ከወንድሟ ልጅ ጋር እራት በልተው አመሻሹ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ተቆጣችኝ በሚል ሰበብ አንገቷን በማነቅ መሬት ላይ በመጣል ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ በሽንኩርት መክተፊያ ቢላዋ የተለያዩ የሰውነት ክፍሏን በመቆራረጥና በመለያየት በሦስት ፊስታል ነጣጥሎ በማሰር ጨለማን ተገን በማድረግና ማንም እንደማያየው በማረጋገጡ አንዱን ፌስታል መፀዳጃ ቤት ሁለተኛውን ደግሞ ለግንባታ የተቆፈረ ቦታ ላይ በመጣል አፈር በማልበስና ሦስተኛውን ፌስታል ግንብ ስር ሊጥልም ችሏል፡፡

ፖሊስ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ ወንጀሉን ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረውን ግለሰብ በመያዝ ቅሪተ አካሎችን የጣለበት ቦታ መርቶ እንዲያሳይ አድርጓል፡፡

የማችን አስክሬን በመሠብሰብ ለቤተሰብ በመስጠት በተከሳሹ ላይ የምርመራ ስራውን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ያጠናቀቀው ፖሊስ የተጠናቀቀውን የምርመራ መዝገብ ለዐ/ህግ በማቅረብና ክስ በማስመስረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ ሻምበል ሙሉጌታን ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ የሞት ፍርድ ውሳኔ ወስኖበታል፡፡

Via: አዲሰ አበባ ፖሊስ


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: