ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የመጨረሻውን ምዕራፍ ውጤታማ ድርድር አድርጋለች – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

- Advertisement -
Sidebar AD

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያስችላትን የመጨረሻውን ምዕራፍ ውጤታማ ድርድር አድርጋለች አሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፡፡

ሚኒስትሩ ለዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የተደረገውን 7ኛውን ዙር የሥራ ላይ ቡድን ስብሰባ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ÷ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል መሆን የሚያስችላትን ውጤታማ ድርድር አድርጋለች ብለዋል፡፡

በ7ኛው የሥራ ላይ የቡድን ስብሰባ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ድል የተገኘበት መሆኑን አንስተው÷ ለዚህ ድል ዋነኛው ምክንያት ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ለ226 የአባል ሀገራት ጥያቄዎች ጥልቅ ምላሾችን የመስጠት፣ የስራ ቡድን ረቂቅ ሪፖርትን የማዳበርና 32 የግዴታ አንቀጾችን የማጠናቀቅ ስራ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡

ከ9 አባላት ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድሮች መጠናቀቁን ጠቁመው÷ በቅርብ ጊዜያት ከአምስት ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ድርድር ስምምነት እንደሚኖር አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከ23 ዓመታት በላይ ድርድር ስታደርግ መቆየቷን አስታውሰው÷ በታዛቢነት በቆየችበት የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን 7ኛ ዙር የሥራ ላይ ቡድን ስብሰባ ላይ መድረሷን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለዚህ ስኬት የበቃችው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ባስገኙት ለውጥ፣ የፋይናንስ ስርዓቱ ክፍት በመደረጉና እንደሀገር በተመዘገቡ ለውጦች መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የተካሄደው 7ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ኢትዮጵያ በድርድር ሂደቱ ላይ ያሳየችውን ቁርጠኝነትና ያስመዘገበችውን ከፍተኛ ስኬት በተሳታፊ አባል ሀገራት እውቅና እንደተሰጠው አስረድተዋል፡፡

8ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ በቀጣይ 2019 ዓ.ም መስከረም ወር እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

FBC




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: