ከውጪ ሀገር ዜጋ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈጸመው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለተጠርጣሪው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 00672 በ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ከውጪ ሀገር ዜጋ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈጸመው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
ተጠርጣሪው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 00672 በሆነ ዴ.ኤክስ ተሽከርካሪ የታክሲ አገልግሎት በመስጠት የሚተዳደር መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም የተለመደውን የታክሲ አገልግሎት ለመስጠት  ለዶክተር ጣሂር ሀሚድ ለተባሉ የሳውዲ ዜግነት ላላቸው ግለሰብ ከቦሌ ኤርፖርት በመጫን ወደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አይሻ መስኪድ እየተባለ ወደ ሚጠራው አካባቢ ጉዞ ያደርጋል፡፡ 
ግለሰቡም ካሰቡበት ቦታ ደርሰው ሂሳብ ከፍለው ይወርዱና ተሽከርካሪውን ይሸኛሉ፤ ነገር ግን ቦርሳቸው ባረጋገጡበት ወቅት ይዘውት የነበረው 3ሺህ የሳውዲ ሪያል የተሰረቀባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
 
‎የግል ተበዳይም የተፈፀመባቸው ወንጀል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለላንቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በማመልከታቸው ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ገንዘቡን ወደ ኢትዮጵያ ብር እንደመነዘረው በቁጥጥር ስር ሊያውለውም ችሏል፡፡
ግለሰቡም ክስ እንደተመሰረተበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያስታወቀ ሲሆን ‎የታክሲ ትራንስፖርት የሚጠቀሙ ተገልጋዮች ህጋዊነት ያላቸውን እና በጥሪ ማዕከሎች የሚገኙ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ መልእክት አስተላልፏል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: