ድምጻዊ አስገኛው አሽኮ (አስጌ ዴንዳሾ) በሴቶች ላይ የሰነዘረው አስተያየት በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆነ​ ታዋቂው ድምጻዊ …

- Advertisement -
Sidebar AD
ድምጻዊ አስገኛው አሽኮ (አስጌ ዴንዳሾ) በሴቶች ላይ የሰነዘረው አስተያየት በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆነ
​ ታዋቂው ድምጻዊ አስገኛው አሽኮ (አስጌ) የሴቶችን የማመዛዘን ብቃትና ትኩረት አስመልክቶ በማህበራዊ ገጹ ያሰፈረው አነጋጋሪ መልዕክት በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ክርክር ቀስቅሷል።
​ድምጻዊው ባስተላለፈው መልዕክት፤ “የሴት ልጅ አዕምሮ ከጭንቅላት ቦታውን ስቶ ኪስ፣ መልክ እና ዳሌ ስር ከተወሸቀ መቼም አያዝንም፣ አያመዛዝንም” ሲል የሰነዘረ ሲሆን፣ ይህም በሴቶች ስነ-ልቦና እና በቁሳቁስ ፍላጎት ዙሪያ ያለውን ምልከታ የነካ ሆኗል።
​አስጌ ይህንኑ መልዕክት ተከትሎ “እቺንማ ወርደን እንነጋገር” በማለት ተከታታዮቹን ለውይይት የጋበዘ ሲሆን፣ በሰነዘረው ሃሳብ ዙሪያ በተለይ በሴት ተከታታዮቹ ዘንድ የተደበላለቁ አስተያየቶች እየተሰነዘሩበት ይገኛል። አንዳንዶች ሃሳቡን ተራ ትችት በማለት እየተከራከሩ ይገኛሉ።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: