አንድም የፌዴሬሽን አመራር ደውሎ “እንኳን ደስ አላችሁ” ባለማለታቸው እኔም ታሪክ የሠሩት አትሌቶችም በእጅጉ አዝነናል

- Advertisement -
Sidebar AD

♦️

♦️አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴና አትሌት ደራርቱ ቱሉ አትሌቶቹ ላባቸው ሳይደርቅ ደውለው መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸው ትልቅ የሞራል ስንቅና መፅናኛ ሆኖናል”
አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ

#Ethiopia | ትናንት ለኢትዮጵያውያንና ለአትሌቲክሱ ልዩና ታሪካዊ ቀን ነበር ማለት ይቻላል፤በማራቶን ታሪክ በወርቅ ቀለም የተፃፉ አዳዲስ ታሪኮች የተመዘገቡበት ልዩ ቀንም ነበር።

ጀግናዋ አትሌታችን ትዕግስት አሠፋ የለንደንን ማራቶንን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በማሸነፍ ክብሯን ከማስጠበቋም በላይ በሴቶች ብቻ(Only Womens)በራስዋ ተይዞ የነበረውን አዲስ የአለም ሪከርድ በማስመዝገብ አለምን ሁሉ ጉድ አሠኝታለች።

በወንዶች የለንደን ማራቶን ሌላ አዲስ ታሪክ በኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻ ተሠርቶ አለም ጉድ ሲል አድሯል፣ውሏል፤

አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በውድድሩ በሁለተኛነት ቢያጠናቅቅም በመጀመሪያ የማራቶን ተሳትፎው ከ2:00:00 በታች ማራቶንን መሮጥ እንደሚቻል ያሳየበትን አዲስ ታሪክ ማፃፍ ቾሏል።

ከእነዚህና ከበርካታ ሪከርድ ሠባሪና ውጤታማ አትሌቶች ጀርባ የሚገኘው አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ ጀግናዎቹን አትሌቶች ደራርቱ ቱሉና አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ሳይቀሩ ሁሉም ከየአቅጣጫው ደስታውን በግል ስልካችንም በኢሜልም እየገለፀ ባለበት በዚህ ሠዓት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች አንዳቸውም በቀጥታ ደውለው ደስታችንን ባለመካፈላቸው አዝነናል፤ከዚህ በፊት ዮሚፍም፣ፎቴንም አለምን ጉድ ያሠኘ ታሪክ አፅፈው ሲመለሱ ኤርፖርት የተቀበላቸው የለም፤ ታሪክ እንደሠራ እንደ ጀግና ሳይሆን እንደ ተራ መግባታቸውን በቁጭት እናስታውሳለን።

አሁንም አንድም አመራር ስልክ ደውሎ ስሜቱን አለመግለፁ አሳዝኖናል፤በዚህም ፌዴሬሽኑ ሊወቀስ ይገባል።

የቀድሞ የፌዴሬሽኑ አመራር ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ስልጣን ላይ እያለች እኮ ስልክ መደወሉን ተወው ያለንበት ወይም ኤርፖርት ድረስ መጥታ ነበር የምትቀበለን፣ደስታችንን የምትጋራው፤አሁን ግን አንድም የአትሌቲክሱ አመራር ደስታችንን ሊጋራ ባለመፍቀዱ በእጅጉ ተሠምቶናል፣በዚህ ወቀሳ እናቀርባለን።ብሏል አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ።

” ከየአቅጣጫው ከማይጠበቁ ሠዎች የእንኳን ደስ አላችሁ ጋጋታ ለእኔም ለአትሌቶቹ ሲመጣ ጉዳዩ በዋናነት የሚመለከተው የአትሌቲክሱ አመራር እስከዚህ ቃለ-ምልልስ ድረስ አንዳቸውም አትሌቶቹጋም ሆነ እኔጋ ደውለው ደስታችንና ታሪካችንን ሊጋሩ፣ሊያበረታቱን ባለመሞከራቸው እጅግ በጣም አዝነናል፣አትሌቶቹም በድርጊቱ ውስጣቸው ተሠብሯል”የሚለው አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ”በኃላፊነት ላይ የሌሉት ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴና ጀግናዋ አትሌት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በኃላፊነት ላይ ሳይሆኑ የተመዘገበው ሪከርድም፣ውጤቱም የሀገር ስኬት ነው ብለው በደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው የአትሌቶቹ ላብ ሳይደርቅ ደስታችንን በትኩሱ መጋራታቸው ሌላ ደስታን ፈጥሮልናል ብቻ ሳይሆን መፅናኛም ሆኖናል፤የኢትዮጵያ ህዝብም እንዲያመሠግንልን እንፈልጋለን”በማለት የበርካታ የማራቶን ሯጮች የስኬታማነት ምስጥር የሆነውና ከእነሱ ስኬት ጀርባ የሚገኘው የሪከርዱ ሸበኛ፣የማራቶን አሠልጣኞች ንጉስ የሆነው ገመዶ ደደፎ።

“እነዚህ አትሌቶች ያስመዘገቡት ታሪክ የሀገር ነው፣በድሉ ስሟ ከፍ ብሎ የሚጠራውም የሀገራችን ነው፤ዕውነታው ይሄ ሆኖ እንዴት አንድ አመራር እንኳን ደውሎ አትሌቶቹን አያበረታታም?እስቲ ኬንያዊያኖችን ምን እያደረጉ እንደሆነ እንዴት ደስታቸውን እየገለፁ እንደሆነ ተመልከት በስልክም፣በእንኳን ደስ አለህ መልዕክትም አጨናንቀውታል፤የእኛ ግን ከዚህ በተቃራኒ በመሆኑ እኔም ልጆቼም ተሠምቶናል፣ውስጣችንም በጣም አዝኗል”ሲል አሠልጠኝ ገመዶ ደደፎ በአስተያየቱ መጨረሻ በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ተናግሯል።በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ አለኝ የሚል አካል ካለ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1