የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከኤ.ኤፍ.ዲ ጋር ውይይት አካሔደ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፈረንሳዩ ልማት ባንክ ኤ.ኤፍ.ዲ (Agence Française de Développement) ጋር በኤሌክትሪክ ዘርፍ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሰፊ ውይይት አካሔዷል።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ተቋማት በመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት፣ በመሠረተ ልማት ማዘመን፣ በአቅም ማሳደግ እንዲሁም ቴክኖሎጂን በሚመለከት ባንድነት ለመሥራት የሚያስችል አጠቃላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ኤ.ኤፍ.ዲ በተለይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራበት የሚገኘውን የኃይል መቆራረጥ ችግርን መቀነስ፣ የኃይል አስተማማኝነትን ማሻሻል፣ የኃይል ብክነትን መቀነስ እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የሥራ ቦታ ደህንነት ጉዳይ በውይይቱ ላይ ከነበሩ አበይት ጉዳዮች መካከል አንደኛው ነው። ሁለቱ ተቋማት የሠራተኞች ደህንነትን ለማሻሻል የሚያግዙ መመሪያዎችን፣ ስልጠናዎችን እና የቴክኒክ ድጋፎችን በጋራ ለማቅረብ ተስማምተዋል፡፡

ኤ.ኤፍ.ዲ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተካሔዱ የኃይል መቆራረጥ ጥናቶች የቴክኒክ እገዛ አድርጓል። በቀጣይ ደግሞ በገንዘብ ድጋፍና በቴክኒክ እገዛ ያልተቆራረጠና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለደንበኞች ማድረስ እንዲቻል ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2