ቤዝ ሪል እስቴት በ16 ወራት የገነባቸውን ዘመናዊ ቤቶች ለደንበኞቹ ሊያስረክብ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​ቤዝ ሪል እስቴት ሙሉ በሙሉ በራሱ ወጪ ያስገነባቸውንና ለኑሮ ዝግጁ የሆኑ (Fully Furnished) ቤቶችን የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለገዢዎች እንደሚያስረክብ አስታወቀ። ተቋሙ ትናንት በብስራተ ገብርኤል በሚገኘው አዳራሹ በሰጠው መግለጫ፣ ግንባታው በጥራትና በፍጥነት ተጠናቆ ለርክክብ መብቃቱን አረጋግጧል።

​የቤዝ ሪል እስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ት ዙልፋ አህመድ እንደገለጹት፣ ይህ የርክክብ መርሃ ግብር ተቋሙ በ16 ወራት ውስጥ የብዙዎችን የቤት ባለቤትነት ህልም በተግባር ያሳካበት የመጀመሪያው ታላቅ ምዕራፍ ነው። ቤቶቹ ከጥራታቸው ባሻገር፣ ለመኖር የሚያስፈልጉ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን አሟልተው የተገነቡ መሆናቸው ከሌሎች ፕሮጀክቶች ለየት ያደርጋቸዋል።

​የፊታችን ቅዳሜ በሚከናወነው በዚህ ደማቅ የርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ባለቤቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ ይጠበቃል።

​ይህንን ታላቅ ኩነት “ሰሙ ኤቨንት እና ማርኬቲንግ” በከፍተኛ ዝግጅት እያከናወነው ሲሆን፣ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ት ሰሚራ ወንድሙ “መርሃ ግብሩ ፍጥነትና ጥራት የተገናኙበት አዲስ ተሞክሮ የሚታይበት ይሆናል” ብለዋል። የሚዲያ ቅንጅት ስራውን ደግሞ ለዓመታት በዘርፉ ልምድ ያለው “ቲኤች ሚዲያ” እያስተባበረው ይገኛል።




Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: