ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ 1 ሺህ 452 ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነውየትምህርት ሚኒስቴር ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 1…

- Advertisement -
Sidebar AD
ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ 1 ሺህ 452 ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው
የትምህርት ሚኒስቴር ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 1ሺህ 452 የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ መሆኑን ገልጿል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ትምህርት ቤቶቹን ሚኒስቴሩ ከክልሎች ጋር በመተባባር በሁሉም ክልሎች አንደሚገነባ ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት ተገንብተው ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዝግጁ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
በዚህም 87 ሺህ 120 ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ያደርጋል ያሉት ሚኒስትሩ÷ የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ጥራት ያለውን ትምህርት ለማዳረስ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑንም አመልክተዋል።
ለዚህም ሚኒስቴሩ ከሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: