3ኛው የጆርካ-ካቫሊኖ የፈረስ ግልቢያ ውድድር ሊካሄድ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በኢትዮጵያ የሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ እና ጆርካ ኢቨንትስ በትብብር ያዘጋጁት 3ኛው የጆርካ-ካቫሊኖ የፈረስ ግልቢያ ውድድር በመጪው ግንቦት 02/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሊከናወን መሆኑን ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።

ውድድሩ በስፋቱም ሆነ በጥራት ካለፉት ዓመታት የተሻለ ሆኖ መቅረቡ የተገለጸ ሲሆን፣ የስፖርቱን ደረጃ ለማሳደግና ተወዳጅነቱን ለመጨመር ታሳቢ ያደረገ ነው።

​በውድድሩ ላይ 8 የሚሆኑ ታዋቂ የፈረስ ግልቢያ ክለቦች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የቤተመንግስት፣ የፖሊስ፣ የመከላከያ እና የዴች ገዳ ክለቦች ይገኙበታል።

በባለፈው ዓመት ​ለአሸናፊዎች የተዘጋጀው የገንዘብ ሽልማት ለ1ኛ ደረጃ 40,000 ብር፣ ለ2ኛ ደረጃ 30,000 ብር እንዲሁም ለ3ኛ ደረጃ 20,000 ብር እንደነበር ተገልጿል። በዚህም ዓመት ዳጎስ ያለ የገንዘብ ስጦታን ጨምሮ ከውጭ ሀገር የመጡ ልዩ ዋንጫዎችና ሜዳሊያዎች ለተሳታፊዎች ተዘጋጅተዋል ተብሏል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የጣሊያን
አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ እንደገለጹት፣ ዝግጅቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የባህልና የስፖርት ግንኙነት የሚያጠናክር ነው። በተለይም እ.ኤ.አ 2026 በጣሊያንና በኢትዮጵያ መካከል በርካታ የዲፕሎማሲና የንግድ ግንኙነቶች የታዩበት ስኬታማ ዓመት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

​አዘጋጆቹ ውድድሩን በቀጣይ በዓመት ሁለት ጊዜ ለማካሄድና ደረጃውን የጠበቀ ዓለም አቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

📸 ከበደ መክብብ

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2