#Ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ በነበረው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት ተቀንሶ የነበረው የናፍጣ ነዳጅ አቅርቦት ወደ ነበረበት እንዲመለስ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ቀደም ሲል በቀን ይቀርብ የነበረው 9 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ በጦርነቱ ሳቢያ በግማሽ ተቀንሶ 4.5 ሚሊዮን ሊትር ብቻ እንዲከፋፈል ተደርጎ መቆየቱን ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።
ሆኖም መንግሥት የሀገሪቱን የምርትና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ በማስገባት አቅርቦቱ በሙሉ አቅም እንዲቀጥል ወስኗል።
ይህንን የአቅርቦት ማስተካከያ ተከትሎ ለመንግሥት የነዳጅ ድጎማ የሚመደበው በጀት በየወሩ የ20 ቢሊዮን ብር ጭማሪ የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህም አጠቃላይ ሀገራዊ የነዳጅ ድጎማውን ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያደርሰው ተጠቁሟል።
የናፍጣ ጭነትን ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ የማጓጓዙ ተግባር ዛሬ የተጀመረ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ደግሞ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ስርጭት እንደሚደረግ ተረጋግጧል።
ይህ እርምጃ በተለይም በግብርና እና በትራንስፖርት ዘርፎች ላይ የሚታየውን እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የላቀ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።
#FuelSupply #Diesel #Economy #Agriculture #Transport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisabab
Source: GetuTemesgen








No comments yet.