ለጤናዎ ጠዋት በባዶ ሆድ ለብ ያለ ውሃ መጠጣት ለብ ያለ ውሃ በባዶ ሆድ መጠጣት ጠቃሚ መሆኑ ይነገራል።ይህን ማደረጉ በጨጓራ …

- Advertisement -
Sidebar AD
ለጤናዎ ጠዋት በባዶ ሆድ ለብ ያለ ውሃ መጠጣት
ለብ ያለ ውሃ በባዶ ሆድ መጠጣት ጠቃሚ መሆኑ ይነገራል።
ይህን ማደረጉ በጨጓራ ዙሪያ ያሉ የደም ስሮች እንዲፍታቱ በማድረግ እና የጨጓራ ጡንቻዎችን በማላላት ቶሎ እንዲነቃና ለቁርስ ዝግጁ እንዲሆን ያደርገዋል።
ጠቀሜታው
ለምግብ መፈጨት ሂደት መፋጠን፦ ለብ ያለ ውሃ የጨጓራና የአንጀት ጡንቻዎች እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ፤ የምግብ መፈጨት ስርአት እንዲጀምር በማድረግ ድርቀትን ይከላከላል።
የጨጓራ አሲድን ለማረጋጋት፦ የጨጓራ አሲድን በማቅጠን /በመበረዝ በጨጓራ ግድግዳ ላይ የሚፈጥረውን የማቃጠል ስሜት ወዲያውኑ ይቀንሰዋል።
እንዲሁም የአሲድ ፍሰትን ወደ ታች በመግፋት በጨጓራና በጉሮሮ መገናኛ አካባቢ የተጠራቀመ አሲድ ካለ፣ ውሃው ጠርጎ ወደ አንጀት እንዲወርድ ያደርገዋል።
የደም ዝውውርን ለማሻሻል፦ የውሃው ሙቀት የደም ስርን እንዲሰፋ ስለሚያደርግ፣ ወደ ጨጓራና አንጀት የሚሄደው የደም ፍሰት እንዲጨምር ያደርጋል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: