#Ethiopia | ከጌዴኦ ዞን ቡሌ ከተማ የተነሳውና የ365 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ የጀመረው የ20 ዓመቱ ወጣት ኢያሱ ክፍሌ የፅናት ጉዞውን አጠናቆ ነገ አዲስ አበባ ይገባል።
ወጣቱ ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበረውን የድል በዓል ምክንያት በማድረግ ለሀገር ያለውን ጥልቅ ፍቅር ለመግለጽ ለሀገር ስለሀገር በሚል መሪ ቃል ጉዞውን ሲያደርግ ቆይቷል።
ኢያሱ ይህንን ረጅም መንገድ ሲያቋርጥ የጠራራ ፀሐይ ሙቀት እና ድንገተኛ ዝናብን የመሳሰሉ የተፈጥሮ ፈተናዎችን በፅናት አልፏል።
የገጠሙት ችግሮች ሳይበግሩት የተስፋ እና የድል ስሜትን ሰንቆ ጉዞውን የቀጠለው ወጣቱ፣ የቡሌ ምድር ያፈራችው የፅናት ተምሳሌት መሆኑን በተግባር አሳይቷል።
የኢትዮጵያን እምብርት አዲስ አበባን ለመርገጥ ጥቂት ሰዓታት ብቻ የቀሩት ሲሆን፣ ልዩ ልዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሚዲያዎች እንዲሁም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የጀግናውን ወጣት አቀባበል ለመዘገብና ታሪኩን ለዓለም ለማጋራት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
ይህ ጉዞ ተራ የእግር ጉዞ ሳይሆን የወጣቶች የሀገር ፍቅር መግለጫና በትውልድ መካከል ያለውን ትስስር የሚያጠናክር ተግባር ተደርጎ ተወስዷል።
ወጣቱ ኢያሱ ክፍሌ ለሀገር የሚከፈል መስዋዕትነት በዕድሜ እንደማይወሰን ያስመሰከረ ሲሆን፣ ነገ አዲስ አበባ ሲገባ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እንደሚጻፍ ይጠበቃል።
#የእግር_ጉዞ #የፅናት_ጉዞ #የሀገር_ፍቅር #ጌዴኦ #ቡሌ #ኢያሱ_ክፍሌ #ድል_በዓል #አዲስ_አበባ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.