በበልግ ወቅት የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት እና የሌሊት ወበቅ ትኩረት እንደሚሹ ተገለጸ በበልግ ወቅት በመደበኛነት ትኩረት ከሚሹ የአየር…

- Advertisement -
Sidebar AD
በበልግ ወቅት የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት እና የሌሊት ወበቅ ትኩረት እንደሚሹ ተገለጸ
በበልግ ወቅት በመደበኛነት ትኩረት ከሚሹ የአየር ሁኔታ ክስተቶች መካከል በቀን የሚታየው ከፍተኛ የሙቀት መጠንና በሌሊት የሚኖረው ወበቅ ዋነኞቹ መሆናቸውን የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃዎች አመልክተዋል።
በተለይም በሜይ ወር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ውስጥ ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል ጋር ተያይዞ በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሙቀት መጠኑ ከፍ ብሎ እንደሚቀጥል ተገልጿል። በዚህም መሠረት በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝ እና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በ32 እና በ39.6 ዲግሪ ሴልሺየስ መካከል እንደሚሆን ይጠበቃል።
ከቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በተጨማሪ በሌሊት የሚታየው ወበቅ ሌላኛው የአየር ሁኔታ ባህሪ ሆኖ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን፣ ህዝብና የሚመለከታቸው አካላት እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1