የቡናው አንጋፋ ተጫዋች ተስፋዬ መኮንን (ጅማ) ከዚህ ዓለም ተለየ

- Advertisement -
Sidebar AD

#።Ethiopia | ​የኢትዮጵያ ቡና ቀድሞ ተጫዋች ተስፋዬ መኮንን “ጅማ” ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል።

​በጅማ ቡና ተክል ክለብ በነበረው ድንቅ ብቃት ወደ ቡና ገበያ (ኢትዮጵያ ቡና) ያቀናው ተስፋዬ፣ በግራ መስመር ተጫዋችነቱና በነበረው ልዩ ተሰጥኦ በ1980ዎቹ የእግር ኳስ ወዳጅን ቀልብ የገዛ ተወዳጅ ተጫዋች ነበር።

ባለ ትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።

​ ነገ ዓርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በሜክሲኮ ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የቀብር ስነ-ስርዓቱ ይፈጸማል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰብ ትልቅ ኮከቡን አጥቷል። በዛ ድንቅ ዘመን በግራ መስመር የሚያሳየው ፈጣንና ቴክኒካዊ ጨዋታ በብዙዎቻችን ትዝታ ውስጥ ሁሌም ይኖራል። ለባለቤቱ፣ ለልጁና ለመላው የቡና ደጋፊዎች መጽናናትን እመኛለሁ። ተስፋዬ መኮንን (ጅማ) በሰራው ስራ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል።

​ተስፋዬ ሆይ! በሰላም እረፍ! 🙏🕊️

***
በወርቃማው ዘመን፤ የእግር ኳስ ጥበበኛ ተስፋዬ (ጂማ) ኳሷ እግሩ ሥር ናት።

​#getu #EthiopiaBunna #TesfayeMekonnen #Jimma #EthiopianFootball #Legend #RestInPeace #ኢትዮጵያቡና #ተስፋዬመኮንን #ጅማ #እግርኳስ #ዜናእረፍት #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1