ቻይና ሙሉ በሙሉ በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ባቡሮችን ይፋ አደረገችበማዕከላዊ ቻይና ሁቤይ ግዛት ውስጥ የሚገኘው እና በእስያ አህጉር…

- Advertisement -
Sidebar AD
ቻይና ሙሉ በሙሉ በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ባቡሮችን ይፋ አደረገች
በማዕከላዊ ቻይና ሁቤይ ግዛት ውስጥ የሚገኘው እና በእስያ አህጉር ረጅሙ ክበባዊ የሜትሮ መስመር ተብሎ የሚታወቀው የውሃን ሜትሮ 12 አዳዲስና ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ የሆኑ ባቡሮቹን ማክሰኞ ዕለት በይፋ አስተዋውቋል።
ይህ 59.9 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ታሪካዊ የሜትሮ መስመር እጅግ ዘመናዊ በሆነ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው።
ባቡሮቹ የላቀ አውቶማቲክ የመንዳት ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ ሲሆን፣ ይህም ያለ አሽከርካሪ እርዳታ ሞተራቸውን በራሳቸው ማስነሳት፣ ጉዞ ማድረግ፣ መታጠፍ፣ ወደ ማቆሚያ መመለስ እና በተጠንቀቅ መቆም እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የባቡሮቹን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በርቀት መከታተልና መቆጣጠር የሚያስችል ዘመናዊ አሠራር ተገጥሞላቸዋል።
ፈጣን እና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጁት እነዚህ አዳዲስ ባቡሮች፣ በሰዓት ከፍተኛው እስከ 80 ኪሎ ሜትር ፍጥነት የመጓዝ አቅም አላቸው።
እያንዳንዱ ባቡር በተሟላ አቅሙ አገልግሎት ሲሰጥ በአንድ ጊዜ እስከ 2 ሺህ 592 መንገደኞችን የማጓጓዝ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ፒፕልስ ዴይሊ ቻይና በዘገባው አመላክቷል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: