#Ethiopia | ታዋቂው የናይጄሪያ የንግድ ተቋም ዳንጎቴ ግሩፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያስፈልገውን የአውሮፕላን ነዳጅ ለማቅረብ ከስምምነት ላይ መድረሱ ተገለጠ።
በአፍሪካ ግዙፍ ተብሎ የሚጠራው የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ስራ መጀመሩን ተከትሎ አየር መንገዱ ከኩባንያው ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት ለማጠናከር መወሰኑ ታውቋል።
ይህ አዲስ አጋርነት አየር መንገዱ የነዳጅ አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግና በናይጄሪያ ለሚያደርጋቸው በረራዎች የሚያስፈልገውን ግብዓት በቀላሉ ለማግኘት ያስችለዋል።
ስምምነቱ በሁለቱ የአፍሪካ ግዙፍ ተቋማት መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ከማሳደጉም በላይ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትብብርን ለማጎልበት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።
#aviation #dangote #business #ethiopianairlines #jetfuel #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.