#Ethiopia | በተደረገው የግማሽ ፍፃሜ የእግር ኳስ ግጥሚያ የጋዜጠኞች ቡድን አርቲስቶችን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ለዋንጫ ማለፉን አረጋግጧል።
በዚህ ጨዋታ ሙባረክ ፋንታው ድንቅ ብቃቱን በማሳየት የዕለቱ ኮከብ ተጫዋች መሆን ችሏል።
በሌላ በኩል ደግሞ የቲክቶከሮች ቡድን የድምፃውያንን ቡድን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።
በዚህ ጨዋታ ያኪ ለቲክቶከሮች ቡድን ባሳየው እጅግ አዝናኝ እና የተሳካ እንቅስቃሴ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል።
በመሆኑም በመጪው እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት በሚገኘው የኤፍቢኢ ሜዳ የጋዜጠኞች ቡድን ከቲክቶከሮች ጋር ለዋንጫ የሚያደርጉት ታላቅ ፍልሚያ ይጠበቃል።
#የስፖርትዜና #እግርኳስ #ቲክቶክ #ጋዜጠኞች #አዲስአበባ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen









No comments yet.