#Ethiopia | የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፣ በአዲስ አበባ ቃሊቲ ገብርኤል የሚገኘውን G+2 እና ቴራስ ያለዉ ቅንጡ ፣ ዘመናዊ ፣ ብዙ ክፍሎች ያሉት ፣ ጥራቱን እና ደረጃዉን የጠበቀ በ544 ካ.ሜ ላይ ያረፈ ቤት ሙሉ በሙሉ ለመቄዶንያ ገቢ ሆኗል!!
ይህ ቤት ከ20 ዓመት በፊት 4 ሚሊዮን ባልሞላ ብር እንዲህ ዉብ ሆኖ የተገነባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን 120 ሚሊዮን ብር ይገመታል፡፡
ይህ ቤት ወላጆቻቸዉን ላጡ ህፃናት እና አረጋዉያን ታስቦ የተሰራ ቤት ሲሆን ከ20 ዓመት በላይ እየተከራየ የኪራዩን ገንዘብ ለአረጋዉያን እና ለወላጅ አልባ ህፃናት ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል!!
ብፁዕነታቸዉ ያሳዩን ደግነት ፣ ርህራሄ ፣ ለአረጋዉያን ያሳዩት ከአዕምሮ በላይ የሆነ ደግነት ሌሎች ደጋግ ኢትዮጵያዉያን የልግስና እጆቻቸዉን እንዲዘረጉ በር የሚከፍት ፣ አብነት ፣ ምሳሌ ተደርጎ የሚወሰድ ተግባር ነዉ!!!
ይህን ድጋፍ ያደረኩት ለኢትዮጵያ ፣ ለኤርትራ ህዝብ ነዉ ፣ መቄዶንያ ትንሿ ኢትዮጵያ ናት ያሉት አባታችን ሁላችሁም እግዚአብሄርን አገልግሉ ፣ ካላችሁ ላይ ስጡ ፣ ገንዘብ እያሰባሰባችሁ በመደገፍ የበረከት ስራ ስሩ ሲሉ አፅንተዉ ተናግረዋል፡፡
ይህንን ዉብ የሆነ ቤት አንፀዉ ያስደመሙን የብፁዕነታቸዉ ወንድም ኢንጅነር አማኑኤል እኔስ ይህ በረከት እንዴት ይቀርብኛል በማለት የበኩላቸዉን ድጋፍ አድርገዉልናል ልግስና ከቤቱ ነዉ ስለተደረገልን ነገር ከልብ እናመሰግናለን!!
እስካሁን መቄዶንያ አጠቃላይ 56 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ይህንን ግዙፍ የሆነ ቤት ተጠቅመን 1 ቅርንጫፍ ጨምረን ወደ ፊት 57 ቅርንጫፍ የሚኖረን ሲሆን የዚህ ቤት እርክክብ የሚከናወነዉ እሁድ ግንቦት 2 ሲሆን የሚዲያ አካላት እንዲሁም ማገዝ የምትፈልጉ ሁላችሁ ቃሊቲ ገብርኤል እንገናኝ፡፡
ስለተደረገልን መልካም ነገር በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን!!
እግዚአብሄር ያክብርልን!!
#መቄዶንያ
Source: GetuTemesgen








No comments yet.