#FastMereja I የሸገር ከተማ አስተዳደር ሁሉን አቀፍ ከተማ የመሆን ራዕዩን ለማረጋገጥ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕከል ያደረገ የቤት ልማት እና የከተማ ግብርና ፕሮጀክቶችን በስፋት እየተገበረ መሆኑን ገለጸ።
የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ገልገሎ ዛሬ በገላን ጉዳ ከተማ አስተዳደር በተካሄደው የመስክ ምልከታ ላይ እንደገለጹት፤ ከተማዋ የሀብታም ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል እንደ አቅሙ የሚኖርባት እንዲትሆን እየተሰራ ነው ብሏል።
ዝቅተኛ ወጪ ቤቶች በገላን ጉዳ ለ80 አባወራዎች የተገነቡ ቤቶች ተጠናቀው የተሰጡ ሲሆን፣ ይህ ሞዳሊቲ በሁሉም ሰብ-ሲቲዎች እንዲስፋፋ ይደረጋል፣ የብሄር ብሄረሰቦችን ስብጥር በጠበቀ መልኩ ለነዋሪዎች እንደሚከፋፈል ተገልጿል።
የምግብ ዋስትና በተመለከተ ከተሞች የገጠር ምርት ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆኑ ራሳቸው “የምርት ማዕከል” መሆን እንዳለባቸው ተመልክቷል። በዚህም የከተማ ግብርና፣ የዶሮ እና የከብት እርባታን ያካተቱ የኢኒሼቲቭ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ነው።
የከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸው እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የከተማ ነዋሪውን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል ባለፈ፣ ሸገርን የኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ የታለሙ እንደሆኑ ነው የተነገረው።



Source: FastMereja








No comments yet.