የሕውሓቱ ጀነራል የፌዴራል መንግስቱ ላይ ዛቱ፡፡ ብልጽግናን ለማስወገድ ተዘጋጅተናል ሲሉ በአደባባይ ወጥተው ተናግረዋል፡፡ የጀነ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የሕውሓቱ ጀነራል የፌዴራል መንግስቱ ላይ ዛቱ፡፡
ብልጽግናን ለማስወገድ ተዘጋጅተናል ሲሉ በአደባባይ ወጥተው ተናግረዋል፡፡ የጀነራል ታደሰን እንቅስቃሴ እግር በእግር እንዲከታተሉ ትእዛዝ የተሰጣቸው እኚህ ጀነራል፤ ሁሉም ነገር አልቋል በቅርቡ ጠብቁን ብለዋል፡፡ ይህ የጀነራሉ ዛቻ የተሰማው ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ ህብረት ጦርነት እንዳይፈነዳ እያስጠነቀቁ ባለበት ወቅት ነው፡፡ 
የሕውሓት ፖለቲካዊ አመራሮች እና ወታደራዊ አዛዦች 4ኪሎ ላይ የሚያሰሙትን ዛቻ ቀጥለውበታል፡፡ ከሰሞኑ የቡድኑ አመራር አዲስአለም ባሌማ ‹‹ለሁሉም ነገር ተዘጋጅተናል፤ ሎጀስቲክ አዘጋጅተናል፤ከፋኖም ከሻብያም ጋር ተጣምረናል›› ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ ዛሬ ደግሞ ከሕውሓት ወታደራዊ አዛዦች መሀል አንዱ የሆኑት የአርሚ 60 አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ህንፃ ወልደጊዮርጊስ ብልጽግናን ለመጣል ተዘጋጅተናል የሚል ከፕሪቶሪያ ስምምነት ያፈነገጠ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ጀነራሉ የህወሓት ልሳን ለሆነው ወይን ሚዲያ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት ማብራሪያ፣ “ማንም መጠራጠር የሌለብት ሁሉም ነገር አልቋል” ሲሉ ፉከራ አሰምተዋል፡፡ ጀነራሉ ብዙዎች ተሰውተውለታል ያሉትን  በተናጠል ክልላዊ ምርጫ የተመሰረተውን፣ የህወሓት መንግሥት መመለስ የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
የሁለት ዓመቱን ደም አፋሳሽ ጦርነት መሬት ለማስመለስ ሳይሆን፣ 2.8 ሚሊዮን ህዝብ የመረጠጠውን መንግሥት ለማስመለስ ነው ያሉት ጀነራሉ፤ በጦርነቱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ሰው ሞቷል የሚባለውን አስተባብለው፤ “አንድ ሚሊዮን ሰው ሞቷል የሚለውን ተውት፣ የተገደሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ጀነራሉ መስዋእት ከፍለንበታል ያሉትን ህወሓት መራሹን መንግሥት ለመመለስ ሙሉ ዝግጁ አለን ብለዋል፡፡ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል ተብሎ ከፍተኛ ስጋት ስለፈጠረው ውጥረት ማብራሪያ የሰጡት ጀነራሉ፣ “ድጋሜ ከተዋጋን የነብረውን መንግስት ለመመለስ ነው” ይላሉ፡፡
የፕሪቶሪያው ስምምነት ከዚህ በኋካ ዋጋ እንደሌለው የገለጹም ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ ወደኋላ የሚመለስን ኃይል የለም ብለዋል፡፡ የፌደራል መንግሥት በስምምነት ሰበብ ትግራይ ከፋፍሏል በማለት የከሰሱ ሲሆን፣ እንደ ጌታቸው ረዳ ያሉ ግለሰቦችንም  እንደ ጠላት እንታገላቸዋለን ብለዋል፡፡
ጀነራሉ ትግራይ ከድተዋል ያሏቸውን ኃይሎች ከፌደራል መንግሥት ጎን ተሰልፈው፣ የህወሓት አመራሮችን ለማጥቃት እየተዘጋጁ ነው በማለት ከሰዋል፡፡ በዚህም የህወሓት አመራሮች የጥቃት ኢላማ በመሆናቸው በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳይችሉ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን፣ በእነ ደብረጽዮን በኩል ከወዲሁ ደብብቆሽ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
ከባለፈው ጦርነት ተምረናል ያሉት ጀነራሉ፣ ዳግም ውጊያ ከተቀሰቀሰ እንደበፊቱ በቀላሉ እጅ አንስጥም ብለዋል፡፡ የህወሓትን መንግሥት በመመለስ የቤት ሥራችንን ጨርሰናል ያሉት እኚሁ ወታደራዊ አዛዥ፣ ቀጣዩ ጉዞ የትግራይን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር ነው ብለዋል፡፡
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: