ኢትዮጵያዊቷ ጀሚላ ተሰማ በታዋቂው የፔንክራፍት (PenCraft) የዓለም አቀፍ መጽሐፍት ሽልማት አሸናፊ ሆነች

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ጀሚላ ተሰማ የተዘጋጀው “የሚዛናዊ ሕይወት ጆርናል” (The Balanced Life Journal) በአሜሪካ ላስ ቬጋስ በተካሄደው 9ኛው የጸሐፊያን ንባብ (Authors Reading) የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ የክብር ባለቤት ሆኗል። መጽሐፉ በምርጥ የሥነ-ልቦና እና የግል ዕድገት (Best Book for Nonfiction Self-help) ዘርፍ የ“PenCraft Award” አሸናፊ ሆነ።

​የቴክኖሎጂ ባለሙያ እና የ“አመኒም ሶሊዩሽንስ” አይቲ ትምህርት ቤት መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆነችው ጀሚላ ተሰማ፣ ይህን ሽልማት ያገኘችው በሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ጥልቅ ለውጥ የሚያመጣ ሥራ በማቅረቧ ነው። ጆርናሉ ግለሰቦች ሕይወታቸውን በስድስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ እንዲገነቡ የሚያስችል ሳይንሳዊ መመሪያዎችን አካቷል።

​እነዚህም፦

​ጤና እና መንፈሳዊ ሕይወት

​የግል እና የሙያ ዕድገት

​የፋይናንስ አስተዳደር እና ማኅበራዊ ግንኙነት

​ጆርናሉ ከንድፈ-ሐሳብ ባለፈ በጸሐፊዋ እውነተኛ የሕይወት ተሞክሮ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ለየት ያደርገዋል። በዘመናዊው ዓለም የተዛባውን የሕይወት ዘይቤ ለማስተካከል እና የታቀደ ሕይወትን ለመምራት ለሚፈልጉ ሁሉ እንደ መፍትሔ ቀርቧል።

​ይህ ዓለም አቀፍ ዕውቅና የጆርናሉን ተደራሽነት ይበልጥ እንደሚያሰፋው የገለጹት ባለሙያዋ፣ በቀጣይ ሰፋ ያሉ የማኅበረሰብ ስልጠናዎችን እና የተሳትፎ መድረኮችን ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን አስታውቀዋል። ጀሚላ ተሰማ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ካላት ከፍተኛ ተጽዕኖ በተጨማሪ አሁን በሥነ-ጽሑፍ ዘርፍ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ማስጠራት ችላለች።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: