#FastMereja I የሸገር ከተማ አስተዳደር ምስረታውን ተከትሎ ባለፉት ሦስት ዓመታት ያከናወናቸውን ግዙፍ የልማት ስኬቶች ለሚዲያ ባለሙያዎች እና ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ይፋ አደረገ። የጉብኝት መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሸገር ከተማ ከንቲባ አቶ ተሾመ አዱኛ (PhD)፣ ከተማዋ በዕውቀት ላይ የተመሰረተችና በኢኮኖሚ ረገድ ተወዳዳሪ ሜትሮፖሊታን የመሆን ራዕይ ይዛ እየተጓዘች መሆኑን ገልጸዋል።
”ገበሬ መሆን አያፈናቅልም” በሚል መሪ ቃል በታገዘ ዘመናዊ አሰራር፣ የሚታረስ መሬት ከ60 ሺህ ሄክታር ወደ 81 ሺህ ሄክታር አድጓል። ለምርት ሂደት የሚውሉ 19 ሺህ ሼዶች ተገንብተዋል ብሏል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ330 በላይ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የተማሪዎች ቁጥር ከ420 ሺህ በላይ ደርሷል።
ከተማዋን የንግድና የቴክኖሎጂ ኮሪደር ለማድረግ በተነደፈው ዕቅድ 2 ሺህ የሚጠጉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ገብተዋል። ከእነዚህም መካከል ዓለም አቀፍ የመኪና መሸጫ ማዕከል አንዱ ነው።
የካዳስተር ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ለ170 ሺህ ነዋሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ (ካርታ) ተሰጥቷል።
ሸገር ከተማ በ2022 እ.ኤ.አ (2015 ዓ.ም) የተመሰረተች ሲሆን፣ በ160,892 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈችና በ12 ክፍለ ከተማ የተዋቀረች ናት። በአሁኑ ወቅት ከ3.2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት ሲሆን፣ ኮዬ ፈጬ “የሸገር ኮከብ ከተማ” ተብላ ተሰይማለች።
ከንቲባው አክለውም የተመዘገቡት ውጤቶች በዘፈቀደ ሳይሆን በተቀናጀ ፕላን የተመሩ መሆናቸውን ጠቁመው፣ “በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ 30 ዓመት ሠርተናል” ሲሉ የሥራውን ስፋት ገልጸዋል። የሚዲያ ባለሙያዎች እና የማህበራዊ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በተለያዩ የልማት ቀጠናዎች የመስክ ምልከታ አድርጓል።



Source: FastMereja








No comments yet.