የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ አምስት ሰዎች ተገደሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ታጣቂዎች በመኖሪያ ቤት ውስጥ በከፈቱት ተኩስ እናት ከሦስት ልጆቿ ጋር መገደላቸውን ዶይቼ ቬለ ዘገበ።

​በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ በደረሰ የታጣቂዎች ጥቃት አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ዶይቼ ቬለ እንደዘገበው ጥቃቱ የተፈጸመው በኢንሴኖ ከተማ “አየር ጤና” ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ተጎጂዎቹ ተኝተው በነበሩበት መኖሪያ ቤት ውስጥ በመግባት ተኩስ መክፈታቸውን የአይን እማኞች እና የሟች ዘመዶች ገልጸዋል።

ከሟቾቹ መካከል አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት (እናትና ሦስት ልጆቿ) መሆናቸው ተረጋግጧል። ታጣቂዎቹ ወደ መንደሩ እየተኮሱ በመግባት ጥቃቱን ፈጽመው ወዲያውኑ ከአካባቢው መሰወራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ጥቃት አድራሾቹ በአካባቢው በሽፍትነት የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ነዋሪዎች መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1