#Ethiopia | እሱስ (ያሬድ) ለሙዚቃ ምን አጎደለባት? ምንም። ሌት ተቀን እንደለፋላት ነው። ጥበብ እንደሆን ፍሬዋ የሚታየው፣ፍቅሯ የሚገለጸው በቀረቧት ቁጥር ነው። ከሸሿት ፈጥና ትርቃለች። እሹሩሩ አታውቅም።
ያሬድም ሀ ብሎ ፒያሳ ከሚገኘው የከፍተኛ 14 ባንድ ከተቀላቀለና ቆሌው ሳክስ መሳሪያ ላይ ካረፈ ጀምሮ መች ተለይቷት። ያሬድ፣ ያሬድ ሙዚቃ እውቀት ለማከል ቢገባም ልቡ ለሳክስፎን እንደተከፈተ ነው። ይኸው በዘመናት ውስጥ አብረው እንደተቆራኙ አሉ።
በተጓዘበት የሙዚቃ መንገዱ ማሂራ ባንድ፣ መዲና ባንድ ፣ሮሃባንድ፣ ዳዲሞስ የለ ብሔራዊ ቴአትር፣ባይራን ባንድ ሆነ ሚሊኒየም ባንድ ተቆጥረው በማያልቁት ባንዶች ሳክስፎንና ያሬድ እውነተኛ ጋብቻ እንደፈጸሙ አሉ። በመሳሪያ በተቀነባበረ ሶስት አልበሞቹም በማይነጥፈው ትንፋሹ ሳክስፎንን በሙዚቃ ታሪካችን ውስጥ ረቀቅ ብሎ ኩሏታል።
ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባቱ የሙዚቃ ባለሙያው ያሬድ ተፈራ፣ ከአንጋፋዎቹ እስከ ወጣቶቹ የሚወደውን ሳክስፎን አንግቶ ስራቸውን አጅቧል። ከእዚያም አለፍ ሲል በፕሮዲዉሰርነት ጥቂት የማይባሉ ድምጻውያንን ስራ አሳትሟል።
በግሌ በትላልቅ ባንዶች ውስጥ የያሬድን የሳክስፎን ድምጽ በከፍተኛ ስሜቱ አጅቦት ስሰማው የሙዚቃ ረቂቅነቱ ይገለጽልኛል። የሚለው ያሬድ፣ ከሙዚቃ ላለመጉደል “ሙያዊ ፍቅር ፣ ያለመታከት መስራት፣ ራስን መጠበቅ፣ ሙያዊ ስነምግባር ወሳኝነት አለው!” ይለናል።
ያኔ ምንም ያላጎደልክባት ጥበብ ምላሽዋን ትሰጥሀለች። ልክ እንደያሬድ ከፍታው ላይ እንድትገኝ ታደርግሀለች።
ክብር ለሚወዱት ሙያ ዋጋ ለሚከፍሉ፣ለከፈሉ ሁሉ።
በውድነህ ክፍሌ
Source: GetuTemesgen








No comments yet.